Thread 1
የዘውግ መርዝ ተካዮቹ :-
ዛሬ የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ የጣለውን የዘውግ መርዝ ከተከሉት ዋነኞቹ እነማን ናቸው? ምንስ አይነት ሰብእና የነበራቸው ነበሩ? እስቲ ከመካከላቸውየሁለቱን ማንነት ህይወትና ህልፈታቸውን በዚህ ቅጥልጥል እንይ
Thread 2
ዋለልኝ መኮንን ካሳ
በቀድሞዋ ወሎ ጠቅላይ ግዛት አማራ ሳይንት አውራጃ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1938 ዓ.ም የተወለደው ዋለልኝ መኮንን ዋናው ነበር። ዋለልኝ፣ በበርካታ የሚያንቆለጳጵሱት "የትግል" አጋሮቹ "የደሀ ገበሬ ልጅ" ተደርጎ ይሳላል።
Thread 3
ይሁንና በበርካታ ባላባት ዘመዶቹ ታገዞ ብዙም የዚያን ዘመን ገባር ልጆች ያላገኙትን ከፍተኛ ትምህርት በማግኘት ተቀማጥሎ ያደገው ዋለልኝ በደሴ ወይዘሮ ስሕን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በማሳደም ነበር የሽብር ጥንስሱን የጀመረው
Thread 4
የዚህን ወጣት አሸባሪ አዝማሚያ ከጠዋቱ የተረዱት የጊዜው የወሎ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ ደጃዝማች ሰሎሞን አብርሃ (ደጃዝማች ሰሎሞን የአሁኑ የኤርትራ አምባገነን ኢሳያስ አፈርቂ አጎት ናቸው) የወጣቱን እንቅስቅሴ ለመንግስት ፈጥነው አሳወቁ
Thread 5
በተለይ በሱ በተጠነሰሰ ሴራ በተማሪዎች ተቃውሞ ሰልፍ ወቅት የአድማ በታኝ ፖሊስ አዛዥ ሕይወት ላይ በተሰነዘረ ጥቃት የፓሊስ ባለስልጣኑ ሕይወት ቢተርፍም የዚህ ወጣት አካሄድ የፍትህ ፈላጊ ሳይሆን የአጥፍቶ ጠፊ ሽብርተኛ እንደሆነ ግልጽ ወጣ
Thread 5
በዚሁ ምክንያት የአድማው መሪ የነበረው ዋለልኝ ለጥቂት ወራት እስር ቢዳረግም በእድሜው ለጋነት የተነሳ "ይታረማል" በሚል ተለቀቀ። ብዙም ሳይቆይ የ10ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች ለዮኒቨርስቲ ወደሚያዘጋጀው...
Thread 6
በአዲስ አበባ ወደሚገኘው በዕደ ማርያም ትምህርት ቤት ተዛወረ። የ11ኛና 12ኛ ክፍል ትምህርቱን በበዕደ ማርያም ያጠናቀቀው ዋለልኝ በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዮኒቨርስቲ እንደገባ ነበር ከደሴ ይዞት የመጣውን አድመኝነትና ሽብር የቀጠለው።
Thread 7
በዚሁ ሽብርተኛ ባህርይው ዋለልኝ መኮንን 5 አመታት እስራት የተፈረደበት ዮኒቨርስቲ ገብቶ ጥቂት እንደቆየ ነበር። ይሁንና መርዘኛ የዘውግ ጥንስሱን "በኢትዮጵያ ብሔሮች ጥያቄ ላይ" (On Question of Nationalities of Ethiopia) ብሎ "ትግል" (Struggle)
Thread 8
..በተሰኘ የተማሪዎች የመጣጥፍት መዝገብ (Journal) ላይ ካሳተመ ከጥቂት ወራት በሁዋላ ነበር። ምንም እንኳን 5 አመት ቢፈረድበትም የእድሜው ወጣትነት ግምት ውስጥ ገብቶ እንደገና ንጉሱ ምህረት አድርገውለት ከእስር ተፈቶ ቀድሞ "አውራ ጎዳና"..
Thread 9
..በተባለው መስርያ ቤት ተቀጠረ።
እዚህ ላይ የሱን የህይወት ታሪክ ገታ አድርገን ስለ ሽብር ወንጀል አጋሩ በአንድነት ንጹሐንን ለማጥፋት ባይሳካም የተገበሩትን ሁለቱንም በተገቢ ሁኔታ ለሞት የዳረጋቸውን አረመኔያዊ የሽብር ሙከራ እንመልከት
Thread 10
ማርታ መብራቱ ፍሰሐ :-
የቀድሞው በናይጄርያ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሁም በንጉሰ ነገስቱ ፖሊስ ሠራዊት የአዲስ አበባ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ብርጋድየር ጄኔራል መብራቱ ፍሰሐ የመጀመርያ ልጅ የሆነችው ማርታ መብራቱ..
Thread 11
..የተወለደችው በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1943 ዓ.ም በአዲስ አበባ "አምስተኛ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ነበር። የ2ኛ ደረጃ ትምህርቷን የተማረችው አባቷ አምባሳደር በነበሩበት ሌጎስ ናይጄርያና ከዚያ በሁዋላ ደግሞ በቦስተን አሜሪካ ነበር።
Thread 12
እንደዚህ ባለ ቅንጦት ያደገችው ማርታ የዲፕሎማት ልጅ ሆና ትምህርቷን ከተከታተልባቸው ናይጄርያና አሜሪካ ወይ ደግሞ ለእረፍት ከምትሄድባቸው የእናትና አባቷ የትውልድ ስፍራ አስመራ በስተቀር ገጠሪቱን ኢትዮጵያን ስለቬትየትናምና..
Thread 13
..ሶቭየት ሕብረት በምታነባቸው መጽሐፍት በምታውቃቸው ገበሬዎች መነጽር ብቻ ነበር የምታውቀው። በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዮኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት ህክምና ተማሪ የነበረችው ማርታ ከዋለልኝ ጋር የተገናኘችው እዚያው ነበር።
Thread 14
..ብዙዎች ማርታና ዋለልኝ የፍቅር ግኑኝነት እንደነበራችው እንዲሚጠረጠር ሲናገሩ አባቷ ብርጋድየር ጄኔራል መብራቱ ፍሰሐ ስለ ሕይወት ታሪካቸው በጻፉት መጽሐፍ "..ማርታና ዋለልኝ ጠንካራ ግኑኝነት ነበራቸው.." በሚል ሐረግ ብቻ አልፈውታል።
Thread 15
የሆነው ሆኖ ዋለልኝ መኮንንና ማርታ መብራቱ ከሌሎች አምስት የወንጀል ግብረ አበሮቻቸው ጋር የሽብር ውጥናቸውን በአዲስ አበባ ከተማ "ኦርማ ጋራዥ" ተብሎ ይጠራ በነበረ ቦታ እየተገናኙ መዶለት እንደጀመሩ የደህንነት ዶሴ ያመልክታል።
Thread 16
አምስቱ አሸባሪ ግብረአበሮቻቸው የሚከተሉት ነበሩ።
1)ጌታቸው ሐብቴ
2)ታደለች ኪዳነማርያም
3)ተስፋዬ ቢረጋ
4)ዮሐንስ ፍቃዱ
5) አማኑኤል ዮሐንስ
ቁጥር 4 እና ቁጥር 5 የኤርትራ ነፃነት ግንባር (ጀብሐ - ELF) አጎብዳጆች (sympathizers) ነበሩ።
Thread 17
..እነዚሁ 7 አሸባሪዎች እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ህዳር 2 1965 ዓም ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 720 -060B የበረራ ቁጥር 708 ከአዲስ አበባ - አስመራ - አቴንስ - ፓሪስ የሚበር አውሮፕላን የእጅ ቦንብና ሽጉጥ ይዘው ተሳፈሩ
Thread 18
..ከላይ ምስሉ የተያያዘው በእለቱ የታተመው የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በጥልቀት እንደዘገበው አሸባሪዎቹ አውሮፕላኑ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነበር አውሮፕላኑን የመጥለፍ ሽብር ተግባራቸውን የጀመሩት። የጋዜጣውን ዘገባ ለማንበብ👇
Thread 19
የአብራሪው ክፍል በመቆለፉ ወደ አብራሪዎቹ መግባት ያቃተው ብዙዎች አማኑኤል ዮሐንስ የተባለው አሸባሪ እንደሆነ የሚጠረጥሩት ወጣት አውሮፕላኑ መጠለፉን ለመንገድኛው አሳውቆ እሱ የሚፈልገውን ካላደረጉ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ አስፈራራ👇
Thread 20
በአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ በኢትዮጵያ የህዝብ ደህንነት የፀረ-ጠለፋ ቡድን አባላት (Anti-hijacker Task Force) ወዲያውን አሸባሪዎቹን ለማምከን (neutralize) ለማድረግ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ። እነዚህ አሸባሪዎች ፍፁም ለንጹሐን ህይወት👇
Thread 21
..ደንታ የሌላቸው ጀብደኞች መሆናቸውን የሚያመለክተው እየበረረ ያለ አውሮፕላን ውስጥ ፈንጂ መውርውራቸው ነው። ይሁንና ፈንጂው በአውሮፕላኑ የሁዋላ ክንፍ በሚገኘው የመንገደኞች መጸዳጃ አቅራቢያ ቢፈንዳም በህይወት ላይ ጉዳት አላደረሰም👇
Thread 22
..በዚያን ጊዜው መቶ አለቃ (በሁዋላ ብርጋድየር ጄኔራል) ተስፋዬ ሐብተማርያም የተመራው የጸረ ጠለፋ ቡድን እነዚሁ አረመኔ አሸባሪዎች እያደረሱት የነበረውን ጉዳት ለመመጠንና አውሮፕላኑን በደህንነት ለማሳረፍ ከፍተኛ ትግል እያደረገ..
Thread 23
በነበረበት የ25 ደቂቃ ተኩስ ልውውጥ መንገደኞች በሰጡት የምስክርነት ገለጻ (Eye witness discription) እንደተገለጸው ዋለልኝ መኮንን ነው ተብሎ የተገመተ አሸባሪ ተመቶ ሲወድቅ ከአካላዊ ገለጻ ማርታ መብራቱ እንደሆነች የተገመተች አሸባሪ..
Thread 24
እላዮ ላይ በመውደቅ እንደገና ከመመታት ልትከላከልለት ብትሞክርም ሁለቱም ተመትተው ከሌሎች አራት የሽብር አጋሮቻቸው አማኑኤል ዮሐንስ ፣ ዮሐንስ ፈቃዱ ፣ ተስፋዬ ቢረጋና ጌታቸው ሐብቴ ጋር ፍጹም አስፈላጊና ተገቢ ቅጣታቸውን ተቀብለዋል።
Thread 25
ከአሸባሪዎቹ መካከል ክፉኛ ቆስላ በህይወት የተረፈችው በጊዜው "የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት" በሚባል መስርያ ቤት ትስራ የነበረውና እንደ ሌሎቹ አሸበሪ ግብረ አበሮቿ ሁሉ ከሀብታም ቤተሰብ የወጣችው ታደለች ኪዳነማርያም ነበረች።
Thread 26
ታደለች ኪዳነማርያም በሆስፒታል ህይወቷ አልፏል።
በዚያን ወቅት ተገቢውን ቅጣት ከተቀበሉት አሸባሪዎች ቀንደኛው አማኑኤል ዮሐንስ ፣ አሁን የኤርትራ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ዘምህረት ዮሐንስ ታላቅ ወንድም ነበር።
Thread 27
የማርታ መብራቱ አባት ብርጋድየር ጄነራል መብራቱ ፍስሐ በጻፉት መጽሐፍ ልጃቸው ማርታም ሆነች ቤተሰባቸው ፍጹም ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንና ልጃቸውም በማንኛውም ጊዜ የኤርትራ ተገንጣዮች ጋር ግኑኝነት እንዳልነበራት አውስተዋል።
Thread 28
የሰውን ማንነት በደም ጠብታ የመወሰን ባህል ቤተሰቦች እንኳን "ኧረ አይደለንም" ቢሉ "እናንተ ምን ታውቃላችሁ እኛ እንንገራችሁ እንጂ ማን እንደሆናችሁ" የሚሉ ኤርትራዊያን አሁን በዚህ ቅጥልጥል አስተያየታቸውን ሲሰጡ ትመለከቱ ይሆናል። 😀
Thread 29
ወደ ሽብርተኞቹ ስንመለስ እነዚህን አረመኔዎች አንድ አውሮፕላን ሙሉ መንገደኛ አውሮፕላኑ እየበረረ ሳይፈጁ የቀጧቸውን የጸረ ጠለፋ ቡድን አባላት በእጅጉ ያለማመስገንና ያለማድነቅ አይቻልም።
Thread 30
በዚያ የ25 ደቂቃ ትንቅንቅ ምንም ሳይበገር አውሮፕላኑ ውስጥ ፈንጂ እንኳ ፈንድቶ አውሮፕላኑን ቦሌ ዓለምዐቀፍ አየር ማረፊያ ያሳረፈውን ድንቅ አብራሪ የዛሬ 48 አመት እንኳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንኛ አስደናቂ እንደነበር ይመሰክራል።
Thread 31
ዛሬ የእነዚህን አረመኔ አሸባሪዎች ታሪክ እያንቆለጳጰሱ ቅዱሳን እንደሆኑ ሁሉ በተለያዬ መጻህፍትና መገናኛ ብዙሐን የሚጽፉት የዚያን ጊዜው የ"ትግል" ጓደኞቻቸው ፣ ለዚህ ትውልድ ስቃይ እነዚህ አረመኔዎች መነሻ መሆናቸውን ማወቅ አለባቸው።
Thread 32
ዛሬ በእነዚሁ ጀብደኛ እብሪተኛ ጋጠወጥ ሽብርተኞች በተጠነሰሰው ጥንስስ ብዙ መቶ ሺዎች ተፈናቅለዋል፣ ተገለዋል ሀብት ንብረታቸውን አጥተዋል። ሰወች በማንነታቸው እንደ አውሬ ታድነዋል።
Thread 33
ዛሬ ዋለልኝ መኮንን በሕይወት ቢኖር በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊከሰስ የሚገባው እኩይ ነው። በእውነት ግን ሲዖል የሚባል ነገር ካለ ለፈጸመው እኩይ ተግባርና ምክንያት ለሆነው መከራና ስቃይ በእሳት ጋን ዝንት አለም እንደሚነፍር ተስፋ አለኝ።
You can follow @Natberh.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled: