Thread 1
ወንጌለ ብልጽግና (Prosperity Gospal) ምንድን ነው?
ይህ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በአሜሪካ ማቆጥቆጥ ጀምሮ ሀይማኖትን መሰረት አድርጎ ራሱን ወደ እምነት (faith) እና ወደ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም (Political Ideology) ያሳደገ አስተሳሰብ ነው።
Thread 2
..ከመሰረታዊ የእምነት መነሻው የፕሮቴስታንት ክርስትና ቅያስ ታጥፎ (deviates) ወንጌለ ብልጽግና ፣ ንዋይና አካላዊ ጤንነት ብቻ በእግዚአብሔር የተመረጡ ብልጫ ያላቸው ጸጋዎች መሆናቸውን ያምናል። መልካም መሳጭ ንግግሮች፣ "ብሩህ" ብቻ ማሰብ..
Thread 3
..(Positive Speech and Positive thinking) ባለጸጋ እንደሚያደርግና ለሀይማኖታዊና ሀይማኖታዊ ሰባኪዎች ይጠቅማል ለሚሉት ጉዳይ ገንዘብ መስጠትና ማዋጣት የበለጠ እንደሚያከብር እምነቱ ይሰብካል። ከሌሎች የክርስትና እምነቶች በጣም በተለየ መልኩ
Thread 4
ወንጌለ ብልጽግና ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በእምነቱ ተከታዮችና በእግዚአብሔር መካከል ያለ የውል ሰነድ (contract) ነው ብሎ ያምናል። በዚህም መሰረት የእምነቱ መሪዎች ሰባኪዎች የዚህ ውል አስፈጻሚ አቃቢያነ ህግ በመሆናቸው ለነሱ የሚደረግ እንክብካቤ
Thread 5
ጠቃሚና ጥያቄ ውስጥ መግባት የሌለበት ነው ብሎ ያስተምራል። በአሜሪካ የዚሁ እምነት ሰባኪያን በመሆን ከተከታዮቻቸው በተሰበሰበ ገንዘብ እጅግ የከበሩ & #39;ወንጌሉን ለማስፋፋት& #39; በሚል ሰበብ አውሮፕላኖችን ተከታዮቻቸውን ያስገዛሉ።
https://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="👇" title="Rückhand Zeigefinger nach unten" aria-label="Emoji: Rückhand Zeigefinger nach unten">ተመልከቱ
Thread 6
ከላይ በተመለከተው ምስል እንዳያችሁት ፣ እነዚህ ሰባክያን ተከታዮቻቸውን በአነቃቂ ንግግር (inspirational) እና በማይጨበጥ ተስፋ እያታለሉ ያሻቸውን ያህል ለማካበት ቢጥሩም በአሜሪካ ከመገናኛ ብዙሀንና ከታክስ ሰብሳቢ አይን ግን አያመልጡም
Thread 7
ይሁንና ተጽእኗቸውን በተለያየ መንገድ እስፋፍተው ፣ አንዳንድ አሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ሳይቀር በወጥመዳቸው በማስገባት ይህንን የማጨበርበር & #39;ስነ ጥበብ& #39; (Scamming Art) ወደ ሌሎች ሀገራት ለማስፋፋት መንገድ ተከፍቶላቸዋል።
Thread 8
በሀገራችን በኢትዮጵያም በተለይ በደቡቡ ክፍል ይህንኑ በእምነት ስም የማጭበርበር ተግባር አጠንክረው የያዙ የወንጌለ ብልጽግና ሰባክያን እንዳሉ ይታወቃል። ብዙዎች ለነዚህ ሰባኪያን ሀብት ንብረታቸውን በየዋህነት አስረክበው ባዶ ቀርተዋል
Thread 9
እስቲ ደግሞ እንዴት ወንጌለ ብልጽግና እንደቋያ እሳት እየተቀጣጠለ መጥቶ ከአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ህንጻ (Capitol) እስከ አራት ኪሎ እንዴት እንደደረሰ እንይ።
ይህ እምነት ለመስፋፋቱ እንደ መሰረት የሚያየውhttps://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="👇" title="Rückhand Zeigefinger nach unten" aria-label="Emoji: Rückhand Zeigefinger nach unten">መጽሐፍ ነው።
Thread 10
"Gospel of Wealth, by Andrew Carnegie" (የብልጽግና ወንጌል፣ በአንድሩ ካርኒጊ) በተባለው መጽሐፍ ነው። አንድሩ ካርኒጊ የአሜሪካ የፋብሪካዎች ባለንብረት (Industrialist) እና በጎ አድራጊ (Philanthropist) ነበሩ። ምንም እንኳን እሳቸው ይህን ሲጽፉ
Thread 11
ወንጌለ ብልጽግናን እንደ ሀይማኖት እንዲሰበክ ራእያቸው ሆኖ ባይሆንም በተለይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በሰማንያዎቹ በጣም የገነኑት የወንጌለ ብልጽግና ሰባክያን ይህንን የሳቸውን መጽሐፍ መሰረት የማስፋፋያውን እቅድ የተለሙበት ነው።
Thread 12
በተለይ ከላይ ፎቶግራፎቻቸውን የምትመለከቷቸው ፣ ጆል ኦስተን ፣ ቤኒ ሔን ፣ጂሚ ስዋጋርት ፣ ኦራል ሮበርትስ የተለያዮ መጻህፍትን በወንጌለ ብልጽግና ዙርያ በመጻፍና ወደ ተለያዮ በተለይ ወደ አዳጊ ሀገራት እንዲሰራጩ አስተዋጽኦ አድርገዋል
Thread 13
ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ወንጌለ ብልጽግና ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የተሰበከው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1994 በጀርመናዊ የብልጽግና ሰባኪ ሬንሐርድ ቦንኬ በተባለ ሰው ነው። በጊዜው በኢትዮጵያ የነበሩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች..
Thread 14
የሰውየውን የፕሮቴስታንት ሰባኪነት እንጂ ስለብልጽግና ወንጌል እምብዛም እውቀቱ ያላቸው ጥቂቶች ስለ ነበሩ ከላይ በፎቶግራፉ እንደሚታየው በተለይ የመጀመርያ ስብከቱን ብዙዎች ተከታትለውለታል። ይሁንና በተከታታይ ለመስበክ የነበረው እቅድ
Thread 15
በመንግስት ቪዛ ክልከላና በኢትዮጵያ ነባሯ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጥብቅ ተቃውሞ ሳይሳካለት ቀርቷል።
በ thread 11 ምስላቸውን ካየናቸው የወንጌለ ብልጽግና ሰባኪያን መካከል ፣በአሁኑ ወቅት..
Thread 16
በአሜሪካ ሁሉም በሚባል ደረጃ ጾታዊ ጥቃት ከመፈጸም ጀምሮ እስከ ግብር ማጭበርበር በሚደርስ የወንጀል ክስ የተበተቡ እንደነ ኦራል ሮበርትስ አይነቶች ደግሞ እነሱ በህይወት ቢያልፉም ያቋቋሟቸው ተቋሟት (ዮኒቨርስቲዎች) በዚሁ ህግ ጥሰት ክስ
Thread 17
..ህልውናቸው አደጋ ላይ ያሉ ናቸው።
ወንጌለ ብልጽግና በአሜሪካና በታዳጊ ሀገሮች ነው እንጂ ተጽእኖው ብርቱ በአውሮፓ ሀገራት እንደ ቁም ነገር አይቆጠርም። በተለይ የሰሜን አውሮፖ ሀገራት (ስካንዴኔቪያ) እንደ ነውር ነው የሚቆጥሩት።
Thread 18
በአሜሪካ አንዳንድ ባለስልጣናት ይህንን እምነት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳጊ ሀገራት እንዲሰራጭ ቡድን አቋቁመው ይንቀሳቀሳሉ።
ተጽእኗቸውም በጣም ብርቱ ነው።
ይህንኑ በሚመለከት @netflix የሰራውን ጥናታዊ ፊልም ይመልከቱ
ቅንጭብ (Trailer) https://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="👇" title="Rückhand Zeigefinger nach unten" aria-label="Emoji: Rückhand Zeigefinger nach unten">
Thread 19
ከነዚህ ባለስልጣናት መካከል በርካቶች የአሁኑን የኢትዮጵያን መሪዎች ፍጹም ድጋፍ በመስጠት ፣ በማወደስና በማሞገስ ይታወቃሉ። ከነዚህም አንዱ የ #Oklahoma ው ሴናተር ጄምስ ኢንሆፍ ናቸው። ምንም እንኳን ሴናተር ኢንሆፍ ...
Thread 20
ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ከፍተኛ አክብሮትና ፍቅር የነበራቸው ቢሆንም ለአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር @AbiyAhmedAli ያላቸው ቅርበት በብልጽግና ወንጌል ምክንያት መሆኑን ብዙዎች ያምናሉ።
Thread 21
ከላይ ያለው ቅንጭብ የሚያሳየው ፣ እኚህ ሴናተር በምን ያህል ጥልቀት በኢትዮጵያ ፖለቲካ በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስልጣን ዋዜማ እንደተሳተፉ ነው። በአሁኑ ወቅት ሴናተር ኢንሆፍ ይህንኑ ወንጌለ ብልጽግና ወደ አዳጊ ሀገራት
Thread 22
ለሚያስፋፋው የአሜሪካ ባለስልጣናት ቡድን እንደ በላይ ጠባቂ የሚታዮ ጎምቱ ፖለቲከኛ ናቸው። የእርሳቸውና ሌሎች በተለይ ከደቡባዊ አሜሪካ ክፍል ያሉ አጥማቂዎችና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካባቢ ካሉ አንዳንድ ባለስልጣናት ግኑኝነት አስደማሚ ነው
Thread 23
ቀደምት የአብርሃም እምነቶች (አይሁድ ፣ ክርስትና እና እስልምና) መገኛ ከሆነችው ኢትዮጵያ እና ኢትየያውያን እምነት ፍጹም በተቃርኖ ደሀን አጥብቆ የመጸየፍ ፣ እንደሌለ የመቁጠር፣ ብልጭልጭነት ፣ አፈጮሌነት በብሩህ እሳቤ (positivity) ስም..
Thread 24
..ቀቢፀ ተስፋን ይህ የወንጌለ ብልጽግና እምነት እያሰራጨ ይመስላል። ከሁሉም አሳሳቢ የሚመስለው ግን ይኽንን እምነት የሚያሰራጩት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በከፍተኛ ስልጣን ላይ ያሉ "ባለስልጣናት" መሆናቸው ነው።
Thread 25
..ዛሬ ዜጎች ሲገደሉ ፣ የተፈጥሮ አደጋ ንብረትን ሲያወድም ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለስልጣኖቻቸው "..ችግር እንደሌለ ተቆጥሮ በብሩህ ከታሰበ (positive thinking) ችግሩ በኖ ይጠፋል.." በሚለው የወንጌለ ብልጽግና ስብከት ሀገር እየገዙ ይመስላል።
You can follow @Natberh.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled: