Thread - 1
...ብዙ ጊዜ የ"አፋር ሱልጣን" ሲባል ስንሰማ በግርታ "እንዴ?!? ኢትዮጵያ ውስጥ ደሞ ሱልታኔት አለ እንዴ?" ብለን የምንጠይቅ ብዙ ነን። ይህንን thread ከጥቂት አመላካች የyoutube ቪዲዮዎች ጋር አጣምሬ አዘጋጅቻለሁ። ተጋበዙልኝ።
Thread 2
...በኢትዮጵያ ከ1514 ጀምሮ የተመዘገበ ታሪክ ያላቸው ሁለት ሱልታኔቶች ይታወቃሉ። የኢፋትና የሐውሳ። ለዛሬ የምንነጋገረው ስለ ሐውሳ (አፋር) ሱልጣኔት ነው። በ1734 ተመስርቶ በ1936 ያከተመው የአውሳ ሱልጣኔት መናገሻ ከተማውን ያደረገው...
Thread 3..
...በሰሜን ምስራቋ አሳይታ ከተማ ነው። ሱልጣኔቱ የተመሰረተው የአውሳ ኢማም ግዛት (imamate) እና የአዳል ሱልጣን ለመቀላቀልና አንድ ሱልጣኔት ተለቅ ያለ ግዛት ለመፍጠር ባደረጉት ስምምነት ነው። አውሳ፣አሳይታንና አካባቢውን ሲይጠቃልል..
Thread 4
...አዳል ደግሞ የአዋሽን ዳርቻ ይዞ ዛሬ መተሐራ፣ ሚሌ የምንላቸውን ቦታዎች አካቶ እስከ አሰብ ወደብ የሚዘልቅ ነበር። የአውሳ ኢማምና የአዳሉ ሱልጣን ያለምንም ግጭት ግዛቶቻቸውን በስምምነት ካዋሀዱ በሁዋላ የአዳሉ መሪ ዳታ ካዳፎ ..
Thread 5
...እና ሙዳይቱ የሚባለው ጎሳቸው የሱልጣንነቱን ወንበር ያዙ። ከሌሎቹ ጎሳዎች በተለየ የሙዳይቱ ጎሳ ንግድ አዋቂዎችና ተጓዦች በመሆናቸው የጎሳቸው አባላት በርከት ብለው በአምቻና በጋብቻ ሳይቀር ወደ ላይኛው ደንከል (ዛሬ ኤርትራ) ተስፋፉ..
Thread 6
...የአሳይታዎቹ አውሳ ኢማም ግዛት ከንግዱና ከጉዞው ይልቅ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ ስነግባርና ስነመለኮትን በማስፋፋት የተጠመዱ ነበሩ። ሪቻርድ ፓንክረስት እንደጻፉት ይህ በሁለቱ (በአውሳና በአዳል) የተደረገው ስምምነት በሳል ከመሆኑ..
Thread 7
...ሱልጣኖቹ ለረጅም ጊዜ በስልጣን መቆየታቸው ስምምነቱ ፓለቲካዊ መረጋጋትን (stability)እንዳመጣ ያሳያል ብለዋል።
የህዝባቸው መተዳደርያ የንግድ ስራ በመሆኑ መንገድ የሚዘጋ ወይ መንገድ ላይ አቁሞ የሚዘርፍ ሰው ከባድ ቅጣት ይቀጡ ነበር..
Thread 8
....እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1875 በ Werner Munzinger የሚመራው የግብጽ ጦር ኢትዮጵያን ለመውረር ሲመጣ መጀመሪያ የወደቀው በአፋር ሱልጣኖች እጅ ነበር። የጊዜው ሱልጣን መሐመድ ኢብን ሀንፍሬ ሰራዊቱን ድል አርገው እሱን ለሞት ዳርገውታል
Thread 9
...በ ሺ ስምንት መቶዎቹ መገባደጃ የአውሳ ሱልጣኔት ችግር ላይ ወደቀ። አውሮፓውያን አፍሪካን መቀራመት የጀመሩበት ጊዜ ሆነና አውሳንም መፈታተን ጀመሩ። ሙዚንገርን የገደሉት ሱልጣን መሐመድ ኢብን ሀንፍሬ አልፈው ሌላ ሱልጣን ተተኩ..
Thread 10
...አዲሱ ሱልጣን ኢብረሂም ይባላሉ። የስልጣን ዘመናቸው እስከዛሬ ድረስ አነጋጋሪ (controversial) በመሆኑና በተክለጻድቅ መኩርያ የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ "ሱልጣን ኢብራሂም አሰብን የሸጠ" በሚል ፎቶግራፋቸው መገኘቱ "የተዛባ የታሪክ..
Thread 11,
...አተያይ ነው" ብለው ብዙዎች እስከዛሬ ይሟገታሉ። የሆነው ሆኖ በኢጣልያዊያን አሰብን በሙሉ መቆጣጠርና ሱልጣኔቱ ገቢ ምንጭ ማሽቆልቆሉ ተዳከመ። በጊዜው የወሎ ንጉስ የነበሩት ራስ ሚካኤል አሊ (በቅድመ ክርስትና ስማቸው መሀመድ አሊ)..
Thread 12
...ለሱልጣኖቹ ድጎማ ያደርጉ ነበር ይባላል። የልጅ ልጃቸው ልጅ ኢያሱም ከአውሳ ሱልጣን ቤተሰቦች ጋር በአጠቃላይ ከአፋር ህዝብ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ነበራቸው።
የአውሳ ሱልጣኔት በዚህ ሁኔታ እንዳለ ኢጣልያ በ1936 እኤአ ኢትዮጵያን ወረረች
Thread 13
...ኢጣልያዊያን ሱልጣኔቱን አፍርሰው የቅኝ ግዛት ቢሮ አሳይታ ላይ ከፈቱ። የጊዜው ሱልጣን የነበሩት ሱልጣን ሀሰን ኢብራሂም ባልታወቀ ምክንያት ህይወታቸው በድንገት አለፈ። የኢጣሊያ ገዥዎች የአውሳን ሱልጣኔት በታተኑት..
Thread 14
..የአምስቱ አመት የኢጣልያ ግዛት ሲያበቃና ኢትዮጵያ ዘመናዊ የአስተዳደር ተወረዶችን በጠቅላይ ግዛት በአውራጃና በወረዳ ስታዋቅር የቀድሞውን የአውሳ ግዛት ለማስመለስ የሞከሩት የሱልጣን ሀንፍሬ ቤተስቦች ያልጠበቁት ሆነባቸው..
Thread 15..
.. በርካታ ግዛቶቻቸው ከወሎ፣ከትግራይና ከሸዋ ጋር ተቀላቀሉ። በዚህ ቅር የተሰኙት በጊዜው ወጣት የነበሩት ሱልጣን አሊ ሚራህ ሀንፍሬ ነፍጥ አንስተው ጫካ ለመግባት አንገራገሩ። በብዙ መካሪና አማላጅ እና ድርድር..ማረጋቸው ሳይነካ..
Thread 16
..የቢተውደድ ማእረግ ተጨምሮላቸው አንዳንድ ለሌሎች የተሰጡ ግዛቶቻቸው እንዲመለሱ የህዝባቸው አስተዳዳሪና የበላይ ጠባቂ እንደሆኑ እንዲቆዮና ዘመናዊ አስተዳደር ግን ቀስ በቀስ በአካባቢው እንዲተዋውቅ ስምምነት ተደረሰ..
Thread 17
...ወታደራዊው መንግስት ስልጣን ሲቆጣጠር፣ ምንም እንኳን ሌሎች መኳንንቶችን ሲገድል ሱልጣን አሊ ሚራህን ባይነካቸውም፣ ህዝባቸውን ለሁዋላቀርነት ዳርገዋል ብሎ በይፋ ይወቅሳቸው ነበር። በዚህና በሌሎችም ፓለቲካዊ ምክንያቶች የተቆጡት..
Thread 18..
..ሱልጣን አሊ ሚራህ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ተሰደዱ። የፓለቲካ ድርጅት አቋቁመው በትጥቅ ትግል ደርግን ለመፋለም ቢሞክሩም ጥረታቸው ብዙም ውጤት ሳያመጣ በ1991 የደርግ መንግስት ወድቆ ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ ከ16 አመት ስደት በሁዋላ ተመለሱ..
Thread 19..
...በመጀመርያዎቹ ጥቂት አመታት ልጃቸው ሀንፍሬ አሊ ሚራህ አዲስ በተቋቋመው የአፋር ክልል ፕሬዘዳንት ሆነው ቢሾሙም ከአዲሱ መንግስት ጋር የስልጣኑ ቤተሰቦች ወዲያው ግጭት ውስጥ ገቡ። ከኢህአዴግ ጋር ካቃረናቸው ዋና ጉዳዮች መካከል..
Thread 20
...የአፋር ህዝቦች አንድነት ጉዳይ ነበር። የአፋር ህዝቦች በሶስት ሀገር (ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራና ጅቡቲ) ተከፋፍሎ መኖርና በአስብ ያሉ አፋሮች በሌላ ባንዲራ ስር መሆን ሱልጣን አሊ ሚራህን እጅግ ያስቆጣ ነበር..
Thread 21
..በዚህ ጊዜ ነበር ብዙዎች ዛሬ የሚጠቅሱላቸውን "..እንኳን እኛ ግመሎቻችን የኢትዮጵያን ባንዲራ ይለያሉ.." ብለው የተናገሩት። ብዙም ሳይቆይ ልጃቸው ሀንፍሬ አሊ ሚራህ ከክልል ፕሬዘደንትነታቸው ተነስተው፣በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር..
Thread 22
..ሆነው የተሾሙት። በዚያው ወደ ሀገር አባታቸው እስካረፉበት 2011 ያልተመለሱት ሀንፍሬ አሊ ሚራህ፣ አባታቸው በ2011 ሲይልፉ፣ የአፋር ህዝብ ሱልጣን ተብለው ተሾሙ። በአለ ሲመታቸው በጅቡቲው ፕሬዘዳንት ታደሞ ነበር።...
Thread 23,
..ዛሬ ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ በ74 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
በዚህ አጋጣሚ በአሁኑ ሰአት በአዋሽ ወንዝ ሙላት ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የአፋር ህዝብ አደገኛ ችግር ላይ ነው ያለው። መንግስትና ህዝብ ልዮ ትኩረት...
Thread 24
..ሊሰጠው ይገባል። የአፋር ህዝብ፣ፍጹም ኢትዮጵያዊ፣ ቅን ፣ እውነትኛ ፣ የሌላ ሀቅ የማይሻ ፣ ደፋርና ጀግና ህዝብ ነው። በልማት በኩል የተረሳ ብዙ ሊደረግለት ሲችል ያልተደረገለት ፣ ይህም ሆኖ ግን ባገሩ የማይደራደር ህዝብ ነው።
Thread 25
... አንድ Joshua Goldstein የተባለ ተጓዥ መላ ምት "መጽሀፍ ቅዱስ የንጉስ ሰለሞን ወርቆች & #39;ኦፊርያ" ከሚባል ቦታ ነው የመጡት ይላል። ምናልባት ንግስት ሳባ ወርቆቹን ከአፋር ውስዳለት ይሆናል" ይላል https://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="😀" title="Grinsendes Gesicht" aria-label="Emoji: Grinsendes Gesicht">
Watch starting on 55:10 https://youtu.be/TaDF6rW6t9k ">https://youtu.be/TaDF6rW6t...
You can follow @Natberh.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled: