Thread 1
ሰሞኑን ስለ ደርግ መዝሙሮች በስነዘርኩት አስተያየት ምክንያት የተቆጡ ወዳጆቼን በዚህ thread መካስ ፈልግሁ።
አዝናኝም አስተማሪም ሊሆን ስለሚችል እባካችሁ ሁሉንም ተመልከቷቸው። የመዝሙሮቹ ቅንጫቢ፣ከነግጥሞቹ ቀርበዋል።
Thread 2
..በደርግ መጀመርያው አመት መዝሙሮች በተለይ በቀድሞው ክቡር ዘበኛ ይዘጋጁ የነበሩት ብሩህ ተስፋን የሚያመለክቱ፣አነቃቂ እና አስማሚ (reconciliatory) ነበሩ። በተለይ "ኢትዮጵያ ትቅደም" ለዚህ ላለንበት ጊዜ ትንቢታዊ ግጥሞች ነበሩት።
Thread 3
..እነዚህ መዝሙሮች በጥንቃቄ የተዘጋጁ ደርግን ከህዝብ ጋር በጥሩ ያስተዋውቁ ነበሩ። ነገር ግን፣ ደርግ ከፓለቲካ ተቀናቃኞቹ መሳርያ ሲማዘዝ መረር ማለት ጀመሩ። ከጎን ተሰልፈው ለሚሞቱ፣ሞታቸው ዋጋ እንዳለው ይዘምር ጀመር።
ጥላሁን ገሰሰhttps://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="👇" title="Rückhand Zeigefinger nach unten" aria-label="Emoji: Rückhand Zeigefinger nach unten">
Thread 4
..ብዙም ሳይቆይ ኢትዮጵያ በሱማልያ ስትወረር በጣም ስሜታዊ የሚያደርጉ ሀገራዊ መዝሙሮች በነሻለቃ ክፍሌ አቦቸር፣ተዘራ ሀይለሚካኤል፣ኮሎኔል ለማ ደምሰው ተዘጋጅተው ቀረቡ። እነዚህ መዝሙሮች ዘመን ተሻጋሪ ፍጹም ሀገራዊ ነበሩ።
Thread 5
..ዝነኛ ድምጻዊያን ሳይቀሩ ሀገራዊ መዝሙሮችን መጫወት ጀመሩ። እነዚህ መዝሙሮችም በማርች ባንድ በወታደራዊ ትርኢቶች እየቀረቡ ህዝቡን ለማነቃቃትና በተለይ ደግሞ ህዝባዊ ሚሊሻዎችን ለመልመል ረድተዋል።
መሐሙድ አህመድ ፣ እናት ሀገርhttps://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="👇" title="Rückhand Zeigefinger nach unten" aria-label="Emoji: Rückhand Zeigefinger nach unten">
Thread 6
...ጦርነት ጋብ በሚልበት ጊዜ የአካባቢ & #39;ኪነቶች& #39; ኢትዮጵያንና ጸጋዎቿን የሚያስተዋውቁ መዝሙሮችን ይዘምሩ ነበር።
በዚህ እጅግ ታዋቂ የነበሩት፣ በጊዜው እድሚያቸው ከ14 እስከ 16 የማይበልጠው የጅማ ኪነቶች ጆሮ ገብ (catchy) መዝሙሮች ነበሩ።
Thread 7
..ይሁንና ጦርነቱ እየተራዘመ ሲሄድና፣የደርግ ማእከላዊነት ወደ ግለሰብ አምባገነንነት ሲቀየር፣ መዝሙሮቹ፣ አንድን ሰው (ኮሎኔል መንግስቱን) ወደ ማወደስ ተሸጋገሩ። አንዳንዶቹ ሲዘመሩ እንኳን አሸማቃቂ (cringe worthy) መሆንን አመጡ።
Thread 8
..እነዚህን መዝሙሮች አሰልቺ እየሆኑ ሲመጡና ቀስቃሽነታቸው በመቀነሱ ወታደራዊው መንግስት በህዝብ ተወዳጅ ወደሆኑና የመንግስት ተቀጣሪ ወዳልሆኑ የግል ባንዶች ፊቱን አዙሮ ሀገራዊ ዘፈኖችን እንዲዘፍኑ ማስገደድ ጀመረ።
ነጻነት መለሰhttps://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="👇" title="Rückhand Zeigefinger nach unten" aria-label="Emoji: Rückhand Zeigefinger nach unten">
Thread 9
..ይሁንና አንዳንዶቹ በወታደራዊና በመንግስት የሚዘጋጁት አብዮታዊና ህዝባዊ መዝሙሮች፣ ከፍተኛ ሙዚቃዊ ጥራት ያላችው ስለነበሩ የግል ባንዶቹ በፈቃደኝነት በመሳርያ ብቻ እያቀነባበሩ ይጫወቷቸው ነበር።
ዘራፍ፣ዘራፍ በዋልያስ ባንድ https://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="👇" title="Rückhand Zeigefinger nach unten" aria-label="Emoji: Rückhand Zeigefinger nach unten">
Thread 10
..ይህንን thread እንዳዘጋጅ ላገዙኝ የቀድሞ ሰራዊት አባል መቶ አለቃ ዬሀንስ አረፈአይኔና ሀሳቡን እንዳመነጭ ላነሳሱኝ @Noslata @kefira_dechatu @AbelAsrat11 @RasAligaz @EthiopiK በጣም አመሰግናለሁhttps://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="🙏" title="Folded hands" aria-label="Emoji: Folded hands">
You can follow @Natberh.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled: