THREAD: ቤሩት በድንገተኛ ፍንዳታ ተናውጣ ወደ 2ሺህ ሰዎች መቁሰላቸውንና ከ70 በላይ መሞታቸው ተዘገበ። ኢት/ያን ከቁስለኞቹ ይገኛሉ። የጠሚው መጻናኛ ትዊት በቤሩት ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ቅሬታ ፈጥርዋል። ለምን ብትሉኝ...
#LebanonExplosion #BeirutBlast
በሊባኖስ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ለመንግስታቸው የድረሱልን ጥሪ ማቅረብ ከጀመሩ 10 ወራት ያልፈዋል። ከጥቅምት 2012 ጀምሮ ሊባኖስ በህዝባዊ አመጽ ታምሳ ያገሪቱ ኢኮኖሚ ሾልቆ በርካታ ዜጎች ስራቸውን አጡ፤ ንግዳቸውም ከሰረ።
ስራ ጠፍቶ የኑሮ ውድነት ሰማይ ጋባ። ያገሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ስልጣናቸውን ለቀቁ፤ ብጥብጡ ቀጠለ። በዚህ ወቅት የቤት ሰራተኞች ምግብና የኪራይ ማጣት ጀመሩ። በሊባኖስ 30 ሺህ ዜጎች ያለው የፊሊፒንስ መንግስት ከታህሳስ ጀምሮ ዜጎቹን ማስወጣት ጀመረ።
በግምት ወደ 300 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ ይገኛሉ። ብዙዎቹ ስራቸውን አጥተው ጎዳና ላይ ወጡ፤ ሳይከፈላቸው በባርነት የሚንገላትቱ ነበሩ፤ የሰባዊ መብት ጥሰቱ እየጨመረ ሲመጣ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሉካን ቡድን ወደ ቤሩት ይላካል ተባለ
ዜጎች ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበት መንግስት እንዲያመቻች ቢጠይቁ፤ የተላከው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ የማህበረሰቡን ጥያቄ እንደማስተናገድ፤ "ጋዜጠኞችን እንዳታናግሩ፤ ገጽታችን አታበላሹ" ነገር ተናግረው ተመለሱ። https://twitter.com/ZekuZelalem/status/1244200062772797440
ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ኪራይ መክፈል እያቃታቸው ጎዳና ላይ መውጣት ጀመሩ። መራብ ጀመሩ፤ ለጾታዊ ጥቃት፤ ለድብደባ ተጋለጡ። ለአደጋ ላለመጋለጥ ሲሉ በነጻ መስራቱን የመረጡ ብዙ አሉ። እነዚህ በትንሹ ብንቆጥራቸው በሺህዎች ይሆኑ ነበር።
በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ መመለስ ለፈለጉ ዜጎቹ የ550 ዶላር ታሪፍ አስቀመጠ። ለብዙ ወራት ያለ ደሞዝ በባርነት ሲንገላቱ ለነበሩት የ 5 ወይ የ 6 ወራት ደሞዝ አስረክቡልን ማለታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቶ ነበር።
በየካቲት ወር በሊባኖስ የሚገኘው ማህበረሰብ ለችግሩ መላ ያይገኝለት በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ለመጎብኘት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ወደ ዱባይ አመሩ። በሁለተኛው እለት፤ በአዳራሽ የዜጎች ጥያቄን የሚስተናግዱበት ፕሮግራም ተዘጋጀ
በጉብኝታቸው ወቅት የኢትዮጵያውያን ችግር ለ5 ወራት በተከታታይ መፍትሄ ሳይገኝለት፤ መመለሻ ላጡ ዜጎች 550 ዶላር ክፈሉ ተብለው ነበር። ይሄ ሁሉ ከኮሮናው ወረርሽኝ በፊት ነበር። የህዝብን አደራ ይዛ አብይን ለማግኘት አንድ እህት ከቤሩት ትነሳለች።
በቤሩት ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን የተመሰረተው @EgnaLegnaDWU የተሰኘው የቤት ሰራተኞች ተቆርቋሪ ድርጅት አባላቸው መሰረት ማንደፍሮ @MessiRobiELB ከቤሩት ተነስታ ወደ ኤሚሬትስ ተጉዛ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የቤሩት ማህበረሰብ የድረሱልን ጥያቄን ታሰማለች
ሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ መሰረት፤ የ @fanatelevision ካሜራዎች እየቀረጿት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይን የማነጋገር አጋጣሚውን አግኝታ በሃገሪቱ ያሉት ዜጎች ወደ ሃገራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ትናገራለች። ከታች የሊባኖስ ጋዜጠኞችን የምታስተናግዳዋ ናት።
የዛን እለት የመንግስት የሚዲያ ተቋማት ከ @MessiRobiELB ንግግር አንኳር ነጥቦቿን ቆራርጠው ህግ ወጥ ደላሎች የተናገረችውን ብቻ አስቀርተው ስለ አስከፊው የህዝብ ችግር ወደ ህዝብ የተላለፈ ነገር የለም። ተሰወረ፣ ተቀበረ።
በነገራችን ላይ ሙሉ ጥያቄዋን የሰሙት ጠቅላይ ሚኒስቴር
@AbiyAhmedAli ችግሩን ለመቅረፍና የበኩላቸውን ለማድረግ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ መሰረት ማንደፍሮ ቃል ገቡላት። ቃላቸውን ሳይጠብቁ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዱብዳ ይመጣል።
በነ አልጀዚራ አይተናቸው ነበር፤ በአሽከርካሪው እየዞሩ፤ ለወገን ደራሽ በመሆን የሃገር ስም የሚያስጠራ ተግባር ፈጽመው የመንግስትን ሃላፊነት የተረከቡት ጀግኒት የምንላቸው የቁርጥ ቀን እንቁዎቹ ናቸው። https://twitter.com/ajplus/status/1265215205153353728
እሄንን ለማድረግ የተገደዱት መንግስት እርምጃ አልወስድም በማለቱ ነበር። የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዩ አቶ ሻሜቦ ፊጣሞ "ወደ ሃገር መልሰናችሁ ለምን 110 ምሊዮን ህዝብ ለአደጋ እናጋልጣለን?" የሚል አሳፋሪ መልስ ሰጥተው ነበር። https://twitter.com/AShamebofitamo/status/1253082697594843137
የኢኮኖሚው ችግር እየባሰ ሲመጣ ግፈኛ የሆኑ አሰሪዎች ኢትዮጵያውያን የቤት ስራተኞቻቸውን ቆንስላ በራፍ ላይ መጣል ጀመሩ። የቆንስላው ሃላፊ አቶ አክሊሉ ታጠረ ኮሮናን በመፍራት ዜጎቹን ወደ መጠልያው አላስገባም ስላሉ ውጪ ቀሩ። https://mg.co.za/africa/2020-06-07-abandoned-by-their-employers-ethiopian-domestic-workers-are-left-stranded-in-beirut/
በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ዜጎች ጥያቄ ቀርቦላቸው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ከወራት በፊት የሰጡት መልስ እነሆ። በህግ ወጥ መንገድ ከተሰደዱ ኢትዮጵያዊነታቸውን ማረጋገጥ አንችልም መሳይ ነገር ተናግረው የብዙ ዜጋን ቅስም ሰበሩ። https://twitter.com/ZekuZelalem/status/1258676193659957248
የሚያስብላቸው መንግስት ጠፍተው ጎዳና ላይ የተጣሉት የዜጎቻችን ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መጣ። በአለም ሚዲያዎች ሽፋን ተሰጣቸው። ቆንስላው የአናስገባም አቋሙን አልቀየረም። https://twitter.com/ZekuZelalem/status/1268183298418905088
ቦኋላ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱና መከራቸው መጨረሻ እንዳይኖረው "የአፍሪካ ኩራት" የሆነው አየር መንገዳችን የበረራ ቲኬት ዋጋን ሰማይ ሰቀሉት። ከቤሩት አዲስ አበባ መሄጃ 250 ዶላር የነበረው 1500 እንዲገባ ተደረገ። https://www.middleeasteye.net/news/ethiopia-lebanon-domestic-workers-pay-quarantine
ብዙዎቻችሁ እንደምታስታውሱ፤ የቆንስላው ሃላፊ የነበሩት አቶ አክሊሉ ታጠረ በሊባኖስ የሚገኙ ዜጎቻችን ኮሮና መያዛቸውን ለመደበቅ ጥረው 8 ዜጎች መበከላቸውን እያወቁ ለVOAና ለBBC አንድም ዜጋ በበሽታው አንዳልተጠቃ ተናገሩ። https://twitter.com/ZekuZelalem/status/1260913141535342592
በንግግራቸው ዜጎቹን ለከፋ አደጋ አጋለጡ። ለዜጎቹ ድህንነት የማይጨነቅ ሃላፊዎች መድበው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለዜጎቹ እንግልት መባባስ ምክንያት ሆነዋል። ብሄራዊ ውርደት እስኪሆንና የሃገራችን ገጽታ እስኪበላሽ ጉዳዩን በቸልታ ማየቱን መረጠ።
የሚዲያ ጫናው ስራውን ሰራና በሳምንታት የቲኬት ዋጋ ወደ 280 ተቀነሰ። አሁን ግን የሃጫሉ ሞት ጉዳዩ እንዲረሳ ስላደረገው፤ የቲኬት ዋጋ በአማካዩ ወደ 400 ዶላር አከባቢ ሆኗል። ኮሮና የያዘው ዜጋ የለም ያሉት አቶ አክሊሉም ተተኩ። https://www.middleeasteye.net/news/coronavirus-ethiopia-lebanon-reduce-flight-costs-quarantine-migrant-kafala
የመንግስት አያያዝ አለም መሳለቅያ ነው ያደረገን። አረከሰን። የሀገር ገፅታ ያበላሸ የዜግነት ክብርን ዝቅ ያስደረገ ነው። በ11 ወራት የመከራና የስቃይ ወቅት የማበረታቻ ቃልም አልተሰማም። "ዜጎች ስለመሆናችሁ ማረጋገጫ የለንም" ማለታቸውን ብቻ።
ከጋና ከፊሊፒንስ፤ ከነ ናይጄሪያና ሲመለሱ የኛዎች የሰው መጫወቻ ሆኑ። አብይ ለቤሩት የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የአይዝዋችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸው ለምን የ @EgnaLegnaDWU መስራቿ ባንቺ ይመርን እንዳበሳጨ የምትረዱት ይመስለኛል። https://twitter.com/BanchiELB/status/1290741914753552386
ከፍንዳታው ተርፋ ቤቷን ያጣች አንዲት እህት አናግሬ ነበር። የተጎዱ፤ መሄጃ ያጡም አሉ። በደንብ አልተመረመረም እንጂ የሞቱም ይኖራሉ። ሆስፒታል የገቡ ዜጎች እንዳሉ የእኛ ለኛዋ ጽጌረዳ ብርሃኑ @tsigereda_B አረጋግጣለች፤ ጎብኝታቸው ነበር።
መንግስት ለዜጎቹ ደፋ ቀና ቢል ኑሮ ዛሬ የአመት መከራና ስቃይ ያየው ማህበረሰብ ለድርብ ችግር አይጋለጥም ነበር። ጠቅላዩ የ11 ወራት ዝምታቸውን በመስበራቸው የተደሰተ የቤሩት ነዋሪ ዜጋ አይኖርም ያልኩበት ለዚሁ ነበር። https://twitter.com/AbiyAhmedAli/status/1290739232538009602
ፈጣሪ በሊባኖስ ያሉት ብርታቱን ጥንካሬውን ይስጣቸው፤ ከሁሉ በላይ አሳቢ አያሳጣቸው። ስለመርዘሙ ይቅርታ አድርጉልኝ። Grazie mille🙏🏿
You can follow @ZekuZelalem.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled: