የታችኛውን የአባይ ሸለቆ ከመሰናበታችን በፊት (Thread)
______
ከጣና ሀይቅ ከ800 እስከ 916 ኪሎሜትሮች ርቀት ውስጥ የሚገኘው የታችኛው የአባይ ሸለቆ ከሳምንታት በኅላ ተፈጥሯዊ መልኩን በመተው፣ ቀስ በቀስ ወደ ግዙፍ ሀይቅነት መቀየር ይጀምራል።
______
ከጣና ሀይቅ ከ800 እስከ 916 ኪሎሜትሮች ርቀት ውስጥ የሚገኘው የታችኛው የአባይ ሸለቆ ከሳምንታት በኅላ ተፈጥሯዊ መልኩን በመተው፣ ቀስ በቀስ ወደ ግዙፍ ሀይቅነት መቀየር ይጀምራል።
ወንዙ በዚህኛው ክፍል በነሐሴ ወር በሰከንድ በአማካኝ 5,000 ኪዩቢክ ሜትር የውሃ ፍሰት ሲኖረው፣ የጥቅምት ወር የፍሰት መጠኑ በአማካኝ በሰከንድ 1,500 ኪዩቢክ ሜትር ይደርሳል። በያዝነው ክረምት የውሃ ፍሰቱ ከአማካኝ በላይ እንደሚሆን ተተንብዯል
ይህ ፍሰት ከሳምንታት በኅላ በህዳሴው ግድብ መገታት ሲጀምር፣ ትልቅ ሰው ሰራሽ ሃይቅ መፈጠር ይጀምራል። ሃይቁ ለሚተኛበት ስፍራ የደን ምንጣሮ ስራ ቀደም ብሎ ተጠናቋል።
ይህ ፎቶ ከህዳሴው ግድብ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ 527 ሜትር ከፍታ አለው። በአካባቢው የተከናወነው የደን ምንጣሮ ከባህር ጠለል በላይ እስከ 675 ሜትር ድረስ ያካለለ ነው።
*በነገራችን ላይ በዚህ ክረምት በመከናወን ላይ የሚገኘው የደን ምንጣሮ የሚቀጥለውን ዓመት ታሳቢ ያደረገ ነው።
የግድቡ ግንባታ በታቀደው መሰረት ከተከናወነ፣ በነገው ዕለት (ሰኔ 23/2020) የመካከለኛውን የግድቡ ክፍል 560 ሜትር ይደረሳል። ይህን ተከትሎ ወሃ መያዝ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ መሆን ይጀምራል። https://twitter.com/Ethiopialiveupd/status/1276911186546774021?s=09">https://twitter.com/Ethiopial...
የምንሰናበተው የታችኛው የአባይ ሸለቆ፣ በእርሻ ማሳዎች መካከል ከሚሽሎከለከው የላይኛው አባይ፣ እንዲሁም ከሰው ተገልሎ በአፍሪቃ ግዙፍ በሆኑት ሸለቆዎች ውስጥ ከሚያዘግመው የመካከለኛው አባይ በብዙ ነገር ይለያል።
በዚህኛው ክፍል የሚገኙ የዕፅዋት ዝርያዎችም እጅግ ሞቃታማ በሆነ አካባቢ የሚያድጉና የራሳቸው ልዩ ባህሪ ያላቸው ናቸው። ዕፅዋቶችን በሰው ሰራሹ ሀይቅ ከመጥፋት ለመታደግ፣ 140 የሚደርሱ የዕፅዋት ናሙናዎች በብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ተሰብስበዋል