ከመጋቢት እስከ መጋቢት
ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ሀይለማርያምን ተክተው ስልጣን ሲይዙ::
የውጭ ሚዲያዎች ጠቅላይ ሚንስቴሩን "የመጀመሪያው ኦሮሞ መሪ" እያሉ ሲገልፆዋችው:: (በኢትዮዽያ የመጀመሪያው ኦሮሞ መሪ ጠቅላይ ሚንስቴር አይደሉም)
የአመራር ለውጥ ቢመጣም በአማራ ክልል ተቃውሞው እንደቀጠለ ነበር:: የሚፈቱ እስረኞች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልታወቀም ነበር:: ተጨማሪ እስረኞች እንዲፈቱ ግፊት ሲደረግ::
እንዲፈቱ ከተጠየቁት እስረኞች መካከል እነዚህ ይገኙበታል::
አሜሪካ በወኪሏ በኩል ለህወሀት የሰጠችው ማስጠንቀቂያ:: ከመልእክቱ እንደሚታየው የአሜሪካ ፍላጎት ህወሀት ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ሳይሆን ህወሀት ስልጣን እንዲያካፍል ነበር::
የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ በብሄር ጥያቄ የአቋም እና ትርክት ለውጥ ማምጣቱን ሲያመላክት::
ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ለፓርላማ ያደረጉት ንግግር በአብዛኛው ዝንድ ተቀባይነት ያገኘ ነበር:: ከኤርትራ ጋር ያለው አለመግባባት እንዲያበቃ ጥሪ ሲያቀርቡ::
ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ቃለ መሀላ ሲፈፅሙ::
አሜሪካ በወኪሏ በኩል የሰጠችው ማሳሰቢያ::
ህወሀቶች በመጀመሪያ የስልጣን ለውጥ መኖሩን አምነው መቀበል የተሳናቸው ይመስል ነበር:: ለጠቅላይ ሚንስቴር አብይ የሰጡት የጊዜ ገደብ 6 ወር ነበር::
አምቦ: የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ የመጀመሪያው የሀገር ውስጥ ጉዞ:: ቄሮ ከጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ጎን ነኝ ብሏል ጠቅላይ ሚንስቴር አብይም በርካታ ህዝብ በተገኘበት ቄሮን አመስግነዋል:: ለማ መገርሳም ደመቀ መኮንንም ከጎናቸው ነበሩ::
ጅጅጋ: የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ሁለተኛው የሀገር ውስጥ ጉዞ:: በሶማሌ እና ኦሮሞ ክልል መካክል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት ሲሞክሩ:: የቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ በጉብኝቱ ብዙም ደስተኛ አይመስልም ነበር::
የግንቦት ሰባት አመራር አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈታ ጥያቄ መቅረብ ሲጀምር::
መቀሌ: የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ሶስተኛው የሀገር ውስጥ ጉዞ:: በትግርኛ ንግግር አደረጉ:: "ትግራይ የኢትዮዽያ ሞተርነች:: የትግራይ ህዝብ ወርቅ ነው:: የወልቃይት ጉዳይ የልማት ችግር ነው::" ማለታቸው (የመጀመሪያውን) ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳባቸው::
ጎንደር: አራተኛው የሀገር ውስጥ ጉዞ:: መቀሌ ላይ ተቃውሞ ስላስነሳባቸው ንግግር ማብራሪያ ሰጡ "ካጠፋሁ ብቆነጠጥ ችግር የለም"::
እንዲፈቱ ሲጠየቁ የነበሩ እስረኞች ሲፈቱ::
ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ለመቀሌው ንግግር ይቅርታ መጠየቃችውን ጎንደር መሄዳቸውን እና እስረኞች መለቀቃቸውን ተከትሎ ህወሀት በተለያዩ ቦታዎች ግጭት ሲቀሰቅስ:: ሞያሌ::
አሜሪካ በወኪሏ በኩል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ኮማንድ ፖስት እንዲነሳ ስትጠይቅ::
ያማማቶ ኢትዮዽያ ሲመጣ:: አሜሪካ በወኪሏ በኩል የኢትዮዽያ እና የኤርትራ ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ ስትወተውት::
ያማማቶ ኤርትራ ሲገቡ:: በኢትዮዽያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን ግጭት እልባት ለማስገኘትና በቀጣናው ጉዳይ ላይ ለመነጋገር እቅድ መያዛቸው::
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ ከስልጣን ከመባረሩ በፊት ቤተመንግስት በተደረገ የእራት ግብዣ ላይ ሲገኝ::
አሶሳ:አባይ ግድብ የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ አምስተኛው የሀገር ውስጥ ጉብኝት:: ግድቡን ከጎበኙ በሁዋላ ስለግድቡ ሰጡት የተባለው አስተያየት ብዙዎችን አነጋግሮ ነበር:: ግድቡ በ10 አመትም እይጠናቀቅም::
ኦሮሚያ ተቃውሞ አላቆመም:: በጉጂ ዞን ሚድሮክ ህፃናት ላይ ጉዳት አደረሰ የሚል መረጃ በመምጣቱ ሰላማዊ ሰልፎች መደረግ ቀጠሉ:: መነሻው ግን ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ቤተመንግስት በተደረገ ንግግር ላይ "ምንሊክ ጥበበኛ መሪ ነበሩ" ማለታቸው ሲሰማ ነበር
ከእስር የተፈቱን በቀለ ገርባ እና እስክንድር ነጋን አንድ ላይ ለመቀበል ዝግጅት ቢደረግም በቀለ ገርባ ግብዣውን ሳይቀበሉ ቀሩ:: የግንቦት 7 አመራር አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈጣ መጠየቁም ቀጥሏል::
አሜሪካ በወኪሏ አማካይነት የኢትዮዽያ እና የኤርትራን ግንኙነት ለማሻሻል ማደራደር እንደምትፈልግ ገልፃለች:: በመካከለኛው ምስራቅ የአረብ እና እስራኤል ችግር ታሳቢ ተደርጏል::
ባሌ: የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ስድስተኛ የሀገር ውስጥ ጉዞ:: ምንሊክ ጥበበኛ መሪ ነበሩ ማለታቸውን ተከትሎ በኦሮሚያ ተቃውሞ የገጠማቸው ጠ/ሚ አብይ ባሌ ሄደው የዋቆ ጉቱን ፎቶ ተሸልመዋል::
ግንቦት ሰባት የወቅቱን ሁኔታ በመገምገም የስትራቴጂ ለውጥ ማድረጉን ሲገልፅ:: መንግስትን ከመቃወም ወደመደገፍ የተደረገ ሽግግር ተደርጎ ሊወሰድ በሚችል መልኩ የለውጡ ደጋፊ መሆኑን የሚያመላክት አካሄድ ተጀመረ:ህወሀት በወኪሎቹ ግንቦት 7ን አጣጣለ
ሰማያዊ ፓርቲ የግንቦት ሰባት አመራር አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈታ ሲጠይቅ::
የግንቦት ሰባት ስትራቴጂ ለውጥ እና አንዳርጋቸ ፅጌ እንዲፈታ የሚደረገው ግፊት መጠናከሩን ተከትሎ ኦህዴድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የመዋቅር ለውጥ የሚያጠና ፕሮጀክት ፅፈት ቤት አቋቋመ:የፕሮጀክት ፅፈት ቤቱ የአዲስ አበባን መዋቅር ከልሷል
በተጨባጭ እየመጡ ካሉ እውነታዎች ጋር ራሳቸውን ያስማሙ የህወሀት አባላትና ደጋፊዎች አዲስ አበባን እየለቀቁ ወደመቀሌ መሄድ ጀመሩ::
የአማራ ተወላጆች ከኦሮሚያ በተለይ ቄለም ወለጋ መፈናቀል ጀመሩ:: የቀድሞ ኦነግ መስራቾችም ወደሀገርቤት ለመመለስ መወሰናቸውን አስታውቀዋል:: ኦህዴድ ተፈናቀሉ ስለተባሉት የአማራ ተወላጆች ማስተባበያ ሲሰጥ "ህገወጥ የመሬት ዝርፊያ" ብሎታል::
በውጭ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደሀገር ቤት መመለስ ሲጀምሩ ቀዳሚዎቹ የኦነግ መስራቾች ነበሩ:: ከጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን አዲስ አበባ ሲገቡ ምንም አይነት ችግር አልገጠማቸውም::
በሌላ በኩል የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴ ጥያቄያችን ትኩረት አላገኘም በሚል ትግሉን ቀጥሏል:: "ኮልፌ መስኪድ ፈረሰ" የሚል ወሬ በፌስቡክ መሰራጨቱን ተከትሎ ሙስሊሞች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ::
ጠቅላይ ሚንስቴር ስልጣን ከያዙ በሁዋላ የተከበረው የመጀመሪያው ግንቦት20 አወዛጋቢ ነበር:ኦህዴድ እና የአብዲ ኢሌ ሶህዴፓ በአሉን በድምቀት አክብረዋል:ህወሀት በአሉ መከበሩን እንደስኬት ቆጥሮታል:አብዛኛው ህዝብ ግንቦት 20ን እንደድሮው አላከበረም
ሸራተን በተዘጋጀው የግንቦት 20 በአል አከባበር ላይ ወደሀገርቤት የተመለሱት የኦነግ መስራቾች ተገኝተዋል::
የግንቦት 7 አመራር አንዳርጋቸው ፅጌ በግንቦት ሀያ ከእስር ተፈቷል::
የአንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት በህወሀት ላይ የፈጠረው መደናገጥ በግልፅ የሚታይ ነበር::
በሌላ በኩል ከኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል የሚፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ቁጥር እየጨመረ ሄደ:: ማፈናቀል እንዲቆም ከመጠየቅ ጎን ለጎን ለተፈናቃዮች እርዳታ ማሰባሰብ ተጀመረ::
የኦነግ መስራቾች ጨፌ ኦሮሚያ ተገኝተው ከኦህዴድ ጋ ለመስራት መወሰናቸውን ሲገልፁ ኦኤምኤን ጣቢያም ወደሀገርቤት ለመመለስ መወሰኑን አስታወቀ:የግንቦት7 ስትራቴጂ ለውጥ ይፋ ከሆነ በሁዋላ የታዩት ክስተቶች ከስትራቴጂ ለውጡ በፊት ከነበሩት ይለያሉ
ሳሞራ የኑስን ጨምሮ የህወሀት የመከላከያና ደህንነት ባለስልጣናት በጡረታ ሲገለሉ ህወሀት አብዲ ኢሌን ለመደገፍ እንቅስቃሴ ጀመረ:ጀነራል አደም የደህንነት መስሪያ ቤት ሀላፊ ሆኖ ሲሾም አብንም ተመስርቷል:የህውሀት የመጨረሻው ምእራፍ መዝጊያ ነበር
የኢህአዴግ ስራአስፈፃሚ በኢትዮ/ኤርትራ መካከል የነበረው ችግር እንዲፈታ መወሰኑን ተከትሎ ህወሀት ተቃውሞ አስነሳ:የኢሮብ ህዝብ ውሳኔውን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገም ተብሎ የነበር:ህወሀት በተከታታይ ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ አለ
ትግራይ ክልል በ27 አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ኢሮብ ውስጥ ነበር:ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ መንግስት በኢትዮ/ኤርትራ ጉዳይ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዳያስፈፅም ጠይቀዋል:: የህወሀት ተቃዋሚ ፓርቲነት ምእራፍ የመጀመሪያው ክስተት ነበር
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል የሚፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ቁጥር እየጨመረ ሄደ:: አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት እንዲቆም ሲጠይቅ አብንም መስራች ጉባኤውን ሰኔ 2 ና 3 2010 አካሄደ::
ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም ያሉ የድምፃችን ይሰማ አባላትም በአንዋር መስኪድ ሰልፍ አድርገዋል::
አሜሪካ በወኪሏ አማካይነት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ያሳሰበች ሲሆን የአምነስቲ እንተርናሽናል ሪፖርትን አስመልክቶም አስተያየት ሰጥታለች::
የመቀሌው ተቃውሞ ሰልፍ ቀጠለ ቢን ዛይዲ ኢትዮዽያ መጥቶ ሄደ ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ግብፅ ደርሰው መጡ::
ህወሀት አዲስ አበባ ያደረገውን ተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በሳምንቱ ሰኔ 16 2010 ለጠቅላይ ሚንስቴር አብይ በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ተጠራ:: ህወሀት የድጋፍ ሰልፉ ፀረትግራይ ሰልፍ ነው:: አስተባባሪዎቹም ፀረ ትግሬ ናቸው ሲል ከሰሰ::
ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ለመመለስ ተሞከረ:: በሌላ በኩል በጉራጌ እና ቀቤና መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰው ተፈናቀለ ንብረት ወደመ:: ጥ/ሚ አብይ ግጭቱን የቀሰቀሱት የቀን ጅቦች ናቸው ማለታቸው ትግራይ ክልልን አስቆጣ::
ከሰኔ 16ቱ ሰልፍ በፊት ጠ/ሚ አብይ በፓርላማ ቀርበው የሰጡት ጥያቄና መልስ ብዙ ሰው ተመልክቶታል:: የህወሀት አባል "አሸባሪዎች ለምን ይፈታሉ?" ብለው ሲጠይቁ የተሰጣቸው ምላሽ "አሸባሪው መንግስት ነው::" የሚል ነበር::
የሰኔ 16ቱን ሰልፍ በተመለከተ የህወሀት አቋም ግልፅ ሲሆን በኦሮሞ አክቲቪስቶች መካከል መከፋፈል አመጣ:: "አብይ መንግስቱ ነው" "አብይ ምንሊክ ነፍጠኛ ነው:ሰልፉ የነፍጠኛ ነው" የሚሉ በአንድ በኩል: የሚደግፉ በሌላ በኩል ሆኑ::
አዲስ አበባ ለሰኔ 16 ሰልፍ ዝግጅት::
አሜሪካ በበኩሏ የኤርትራ መንግስት ወደኢትዮዽያ የሰላም ልኡክ መላኩን እንደምትደግፍ በወኪሏ በኩል ገለፀች::
ግንቦት ሰባት የትጥቅ ትግል ማቆሙን በይፋ ሲያውጅ የሰኔ 16ቱን ሰልፍ አስተባባሪዎች በኢሊሊ ሆቴል መግለጫ ሰጡ::
ሰኔ 16: አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ::
ሰኔ 16 መስቀል አደባባይ የፈነዳውን ቦንብ አስመልክቶ ህወሀት የያዘው አቋም::
የኤርትራ ሰላም ልኡክ አዲስ አበባ ገብቶ በኢትዮዽያ እና ኤርትራ መካከል የነበረውን ግንኙነት ለማስቀጠል መክሯል::
ሰኔ 16 አዲስ አበባ የተደረገውን ሰልፍ ተከትሎ በሌሎች ክልሎችም የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ:: አማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል: ደቡብ ከግማሽ በላይ: አፋር: ጅጅጋ:ሀረር:ድሬዳዋ:ጋምቤላ:: ኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ቦታ የድጋፍ ሰልፍ አልነበረም::
ከዳኡድ ኢብሳ በቀር በኦሮሞ ነፃነት ግንባር የተደራጁ ፓርቲዎች ሀገር ውስጥ መግባት ጀመሩ:: ደጋፊዎቻቸውም ቦሌ ድረስ እየሄዱ ሲቀበሏቸው ምንም አይነት ችግር አላጋጠማቸውም::
በአማራ ክልል ባህርዳር የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ተቃውሞ አስነሱ:: በድጋፍ ሰልፉ ላይ የታዩት ረጃጅም ባንዲራዎች በህግ ያልተፈቀዱ ናቸው ተባለ:: በተቃራኒው ወለጋ ላይ ረጃጅም የኦነግ ባንዲራ የያዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ::
በከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ አዲስ አበባ ሲገባ ደጋፊዎቹ የኦነግ ባንዲራን እያውለበለቡ ተቀብለውታል:: ያጋጠማቸው ችግር አልነበረም::
በከማል ገልቹ ሚመራው ኦነግ አዲስ አበባ ሲገባ የተደረገለት አቀባበል ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ቄሮዎች ተገኝተዋል:: ከአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ምንም አይነት ግጭት ውስጥ አልገቡም ነበር::
ከጉጂ ዞን የተፈናቀሉ የጌድኦ ተወላጆችን መልሶ ለማቋቋም እንቅስቃሴ የተጀመረው ዘግይቶ ነበር:: በተደጋጋሚ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉት የጌዴኦ ተወላጆች በመጠለያ ካምፕ::
ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ወደ ኤርትራ ያደረጉት ጉዞ በህወሀት እና የኦሮሞ ብሄርተኞች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም:: በጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ላይ የሚያደርጉት ተቃውሞ መቀናጀት የጀመረው ከዚህ ምእራፍ በሁዋላ ነበር:: የፌዴራሊስት/አሀዳዊ ትርክት መጣ
አሜሪካ በወኪሏ በኩል ኢትዮዽያ እና ኤርትራ የደረሱበትን ስምምነት አደነቀች:: በኤርትራ ላይ የተጣለው ማእቀብ እንዲነሳም ለመጠየቅ ሀሳብ ቀረበ:: የእስራኤል እና አረብ ሀገራት/መካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ ታሳቢ ተደርጏል::
በህወሀት እና የኦሮሞ ብሄርተኞች መካከል ግልፅ የሆነ አሰላለፍ አንድነት የተጀመረ ሲሆን ሁለቱም በሀሳብ ተሸናፊነታቸውን ያመኑበት ነው::
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ኢትዮዽያ ደርሰው ተመለሱ:: የአቀባበል ስነስርአቱ በሲዳማ ባህል ጭፈራ ነበር:: ሚሊኒየም አዳራሽ የነበረው ዝግጅት አወዛጋቢ ነበር:: ቴዲ አፍሮ የተፈፀመበትን ሸር ይፋ አድርጏል:: "የምንሊክ አምላክ ይመስገን" ማለቱ ውዝግብ አስነሳ
የኦሮሞ ብሄርተኞች ከህወሀት ጋር መግጠማቸውን እና በጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ላይ የሚያነሱትን ተቃውሞ: ከህወሀት ጋር ተቀናጅተው የሚቀሰቅስቅሱትን ግጭት ለማባበል በሚመስል ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ሆኖ ተሾመ::
የኢትዮዽያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ መጀመሩን ተከትሎ ለአመታት የተለያዩ ቤተሰቦች ተገናኝተዋል::
ባሌ ጎባ:
"ነፍጠኞች የሀጅ አዳም ሳዶ ሀውልትን አናሰራም አሉ" በሚል ግጭት ተፈጥሮ አንድ ሰው ተገደለ የታጠቁ ቄሮዎች መታየት ጀመሩ:: መከላከያ መሰማራት ጀመረ:: ከባሌጎባ ቀጥሎ ተመሳሳይ ግጭቶች ኦሮሚያ ክልል እየተበራከቱ መጡ::
ኦሮሚያ ክልል በከተሞች ዙሪያ የተደራጁ እና የታጠቁ ቄሮዎች በቀበሌ ሚሊሻ ፖሊስነት እየሰሩ እንደሆነ የሚያመላክቱ መረጃዎች መውጣት ጀመሩ::
የባሌ ጎባ ግጭትን አስመልክቶ መንግስት የሰጠው ምላሽ ግጭቱ ከሀውልት መስራት ጋር እንደማይገናኝ እና በክልሉ የሚፈጠሩ ግጭቶችን መንስኤ ያመላከተ ነበር::
በህወሀትና ኦሮሞ ብሄርተኞች ግንባር ኦሮሚያ ክልል ግጭቶች እንደቀጠሉ ቆዩ:: የጠ/ሚ አብይ የአሜሪካ ጉብኝትም ይፋ ሆነ::አሜሪካም በወኪሏ በኩል ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ለኖቤል ሽልማት እንደሚታጩ ገለፀች:: የእስራኤል እና አረብ ግጭት ታሳቢ ተደርጏል
ጠ/ሚ አብይ እና ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ በኤሜሬትስ ያደረጉት ጉብኝት:: ኒሻል ተሸልመው:: ጠ/ሚ አብይ ከሰይፉ ኢቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ የቢን ዛይድ አድናቂ እንደሆኑ ገልፀው ነበር::
July 26/ 2018
ጠ/ሚ አብይ ወደ አሜሪካ በሚጏዙበት እለት የአባይ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ ተገደለ:: በአማራ ክልል ሰልፎች ተደረጉ::
መንግስት የኢንጂነር ስመኘውን አሟሟት አስመልክቶ ባወጣው የምርመራ ሪፖርት ኢንጂነሩ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ገልፆአል::
ጠ/ሚ አብይ በአሜሪካ ያደረጉትን ጉዞ ጀመሩ:: በድር የሙስሊሞች አለም አቀፍ ጉባኤ እና የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አባቶችን አግኝተዋል::
የኢንጂነር ስመኘውን ግድያ ተከትሎ በመቀሌ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን የክልሉ ፕሬዝዳንት በሰልፉ ላይ የጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ምስል ያለበትን ኮፍያ ለብሰው ታይተዋል:: ህወሀት በግልፅ በመሪው አማካይነት የተቃውዋሚነት መስመር መጀመሩን አወጀ::
በሌላ በኩል ጠ/ሚ አብይ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮዽያውያን ጋር የሚያደርጉን ውይይት በዋሽንግተን ዲሲ ጀመሩ:: አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የአማራ ተወላጆች የኢንጂነር ስመኘው ግድያን ተቃውመው ሰልፍ ሲወጡ ፌዴራል ፖሊስ ሰልፉን በትኗል:: የተጎዱ ነበሩ
የዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ላይ የኦነግ ደጋፊዎችም ኢትዮዽያውያን ሙስሊሞችም ተገኝተው የነበረ ሲሆን የትግራይ ቲቪ የጠ/ሚ አብይ ንግግርን አላስተላለፈም ነበር:: በሌላ በኩል የህወሀት ጀነራሎች መቀሌ መግባታቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች መውጣት ጀመሩ
ሚኖሶታ: የጠ/ሚ አብይ ሁለተኛው የአሜሪካ ጉዞ መዳረሻ:: ከOMN ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድ ጋር:: በሚኖሶታ ውይይት:: በመቀሌ የህወሀት ጀነራሎች ሊታሰሩ ነው የሚል ወሬ በስፋት መሰማት ጀመረ:: ጠ/ሚ አብይ እና ለማ መገርሳ ከኢሳት ዳይሬክተር ጋር ተገናኙ::
ጠ/ሚ አብይ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ሲመለሱ በስደት የነበሩትን ፓትሪያርክ ይዘው ተመልሰዋል:: ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ የምርጫ ቦርድን እንድትመራ ጥያቄ የቀረበላት ሲሆን ግንቦት 7ም ወደሀገቤት ለመመለስ መወሰኑን ይፋ አድርጏል::
የOMN ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድ ወደኢትዮዽያ ተመለሰ በሚሊንየም አዳራሽ በተደረገ አቀባበል ላይ ከንቲባ ታከለ ተገኝተው ምስጋና አቀረቡ:: በሌላ በኩል ሶማሊ ክልል አብዲ ኢሌ ቤተክርስትያን አቃጠለ በርካቶች ተፈናቀሉ::አብዲ ኢሌም በቁጥጥር ስር ዋለ::
ለማ መገርሳ ዳኡድ ኢብሳ እንዲመለስ ለማግባባት ኤርትራ ተላኩ::በጠ/ሚ አብይ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት ዳውድ የለማን ጥያቄ ተቀበሉ::በሌላ በኩል አሜሪካ በሶማሌ ክልል የሚኖራትን ፖሊሲ በወኪሏ ይፋ አደረገች:: የክልሉ ነዳጅ ታሳቢ ተደርጏል
የOMN ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድ የሀገር ውስጥ ጉዞ ከጊንጪ ተጀመረ:: በጊንጪ የተቀመጠው ሀውልት ኦሮሚያ ክልልን ገንጥሎ የሚያሳይ መሆኑ ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳ:: ጉዞው አምቦ ቀጠለ:: ከህወሀት ጋዜጠኛ የመጀመሪያ ቃለ ምልልስ:የአማራ ክልል ጉዞ ጎንደር
ሻሸመኔ: ለOMN ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድ በተዘጋጀ የአቀባበል ስነስርአት ላይ ቦንብ ሊያፈነዳ ነበር የተባለ ግለሰብ በአደባባይ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ:: የክልሉ መንግስት ወንጀሉን ያወገዘ ሲሆን በወንጀሉ የተጠረጠሩ ታስረዋል ተባለ::
የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በህወሀት እና ጠ/ሚ አብይ መካከል እርቅ ለማምጣት ሞከረች:: በሌላ በኩል የግንቦት ሰባትን ወደ ሀገርቤት መመለስ ለመቀበል ዝግጅት ተጀመረ:: የOMN ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድም ለሀጅ ጉዞ መካ ሄዱ::
አዲስ አበባ ለግንቦት 7 አቀባበል ዝግጅት ተጀመረ:: ባንዲራዎች ተሰቀሉ አደባባዮች አረንጏዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ተቀቡ::አብዲ ኢሌ ለፍርድ መቅረብ ሲጀምር የዳኡድ ኢብሳ ኦነግ ወደሀገርቤት ለመመለስ መወሰኑን ይፋ አደረገ::
አዲስ አበባ ለጣይቱ ሀውልት ማሰሪያ የተጣለው የመሰረት ድንጋይ ውዝግብ አስነሳ:ቄሮ ሀውልቱ መሰራት የለበትም አለ:ከንቲባ ታከለ የሀውልቱ ወሬ ውሸት ነው አለ:የአልጀዚራ ጋዜጠኛ መሀመድ አደሞና አዲስ ስታንዳርድም አረጋገጡ:የመሰረት ድንጋዩ ም ተነሳ
አዲስ አበባ: የታማኝ በየነ ወደሀገርቤት መመለስ:: የግንቦት 7 ሀገር ውስጥ መግባትና የተደረገለት አቀባበል:: በህግ ያልተፈቀደ ባንዲራ ውዝግብ ማስነሳቱን ቀጠለ::
አዲስ አበባ: በዳኡድ ኢብሳ የሚመራውን ኦነግ ለመቀበል ዝግጅት:: ቄሮዎች አደባባዮችን በኦነግ አርማ ቀለም ቀቡ:: አስፖልት ላይ "ኦነግ" አደባባይ ላይ "ቄሮ ጃዋር" የሚሉ ፅሁፎችን ፃፉ:: የገጠማቸው ችግር አልነበረም::
የዳኡድ ኢብሳ ኦነግን ለመቀበል በአይሱዙ የተጫኑ ቄሮዎች አዲስአበባ ገቡ:ቄሮዎች ወደምንሊክ አደባባይ ማቅናታቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባ ወጣቶችና በቄሮዎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ:ንብረት ወደመ:ቄሮዎች የምንሊክ ሀውልትን እዲያፈርሱ ሲመከሩ ነበር
መስቀል አደባባይ ለኦነግ አቀባበል በተዘጋጀ ሰልፍ ከንቲባ ታከለ ተገኝተው ፍንፍኔ የኦሮሞ እምብርት መሆኗን የኦሮሞ ህዝብ ለፍንፍኔ መታሰሩን መገደሉንና መሰደዱን ተናገሩ:ፌዴራል ፖሊስ የምንሊክ ሀውልትን ለመጠበቅ ተላከ:ቡራዩ ላይ ጭፍጨፋ ተጀመረ
ቡራዩ የስልጤ ጉራጌ ጋሞ እና አማራ ብሄር ተወላጆች እየተለዩ ተጨፈጨፉ:: በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤት ንብረታቸው ተዘርፎ ተፈናቀሉ:: በሌላ በኩል ኤርትራ የነበረው የዳኡድ ኢብሳ ኦነግ ጦር መቀሌ በህወሀት አመራሮች አቀባበል ተደረገለት::
ከቡራዩው ጭፍጨፋ ያመለጡ ወደ መሀል አዲስ አበባ ተሰደዱ::
አዲስ አበባ የቡራዩውን ጭፍጨፋ ተቃውሞ በተጠራ ሰልፍ አምስት የአዲስ አበባ ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ታፍሰው ጦላይ ተላኩ:: የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት::
ኦነግ ከኦሮሚያ ክልል በሚዋሰኑ ቦታዎች ጥቃት ማድረስ ቀጠለ:: በኢትዮዽያ የተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ::
ኦሮሚያ ክልል መሳሪያ የታጠቁ ህፃናት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት ኦነግን ትጥቅ እንዲያስፈታ ጥያቄ መቅረብ ጀመረ:: ኦነግ ለትጥቅ ፍታ ጥያቄ "ትጥቅ ፈቺ እና ትጥቅ አስፈቺ የለም:: ጉዳዩ ሴንሲቲቭ ነው::" የሚል ምላሽ መስጠቱ::
October 10/2018
የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ:: ጠ/ሚ አብይ ሙከራውን አስመልክቶ ለፓርላማ "መንግስታችን ተነካ ብለው ከቡራዩ ከለገጣፎ አርሶአደር ወጣቶች ተደራጅተው እየመጡ ነበር:: ነገሮች ባይረጋጉ እልቂት ይፈጠር ነበር::" ማለታቸው::
የኦሮሚያ ቤተክህነትን ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩ የፕሬዝዳንት ኢሳያያስ በድጋሚ ወደኢትዮዽያ ደርሶ መመለስ:: የኮዬ ፈጨ ክንዶሚንየም እና የቄሮ ኮንዶሚንየም ይገባናል ተቃውሞ::
የሀይለስላሴ ሀውልት መመረቁን ተከትሎ በለገጣፎ የአማራ ተወላጅ መኖሪያ ቤቶች "ህገወጥ ግንባታ" በሚል መፍረሳቸው:: የአስራት ሚዲያ መቋቋም::
ኦነግን ትጥቅ የማስፈታት ሙከራ: የኦነግ ትጥቅ አልፈታም ምላሽ:: "ብቻዬን ብቀር እንኳ ትግሌን አቀጥላለሁ"
ህወሀት ከስልጣን ከተባረረ በሁዋላ የተከበረው የመጀመሪያው የአድዋ ድል በአል ምንሊክ አደባባይ ብዙ ሰው በተገኘበት መከበሩ:: ለማ መገርሳ "የአዲስ አበባን ዴሞግራፊ እንቀይራለን" ማለታቸውን ተከትሎ የገጠማቸው ከፍተኛ ተቃውሞ::
በአዲስ አበባ የመታወቂያ ካርድ ውዝግብ ማስነሳቱ: የአሜሪካ ኤምባሲ March 10 መስቀል አደባባይ ስለተጠራ ሰልፍ ያወጣው ማስጠንቀቂያ: የቦይንግ 737 አውሮፕላን መከስከስ እና የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት-ባልደራስ መመስረት::
የተፈናቀሉ ጌዴኦ ተወላጆች ሁኔታ የቀሰቀሰው ቁጣ: ግሎባል አሊያንስ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች ያሰባሰበውን ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ማስረከቡ::
የፈረንሳዪ ፕሬዝዳንት ኢትዮዽያን መጎብኘታቸው:: የላሊበላ ጉዞ:: የባላደራው ምክርቤት ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ታከለ ኡማ የገጠመው ፈተና::በውጭ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን ተቃውሞ:: የአዲስ አበባ ውሀ አቅርቦት መቋረጡና የተከሰተው የውሀ እጥረት::
ኦሮሚያ ክልል ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ:: አዲስ አበባ ዙሪያ ፋብሪካዎች መቃጠላቸው:: በሱሉልታ የሻማና ሳሙና ፋብሪካ መቃጠሉ::
አዲስ አበባና ዙሪያው በቡድን የተደራጁ ወጣቶች መሬት መከፋፈል መጀመራቸው::
ውጭ ሀገር በስደት ይኖሩ የነበሩ ሼኾች ኢትዮዽያ መግባታቸው:: የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነአፓ) መመስረት::
በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ተቃውሞ:: የአብያተ ክርስትያናት ቃጠሎ:: በሰላሌ የተቃጠለው ቤተክርስትያን::
ኦሮሚያ ክልል እንዲገነጠል የሚጠይቁ ሰልፎች:: አንቀፅ 39 ተግባራዊ ይሁን:: እኛ ታግለን ሌላው ስልጣን መያዝ የማይገባ ነው::
በአማራ ክልል አጣዬ ከሚሴ የተቀሰቀሰው ግጭት:: የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ከማል ገልቹ ከስልጣን መነሳታቸው::
ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም ያሉ ሙስሊሞች ተቃውሞ መቀጠላቸው:: የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙ::
በጉራጌ ለ158 አመታት ተቋርጦ የነበረው የኦሮሞ ገዳ ስርአት በድጋሚ ተቋቋመ መባሉ የቀሰቀሰው ተቃውሞ:: ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ በአማራ ክልል ወሎ ያደረጉት ጉብኝት:: "ክልሎች የሰጠናቸውን በጀት ሚሊሻ ሚቀልቡበት ከሆነ ልማት ከየትም አይመጣም"
"ከ500 አመት ወዲህ በታሪካችን እንዲህ ያለ ፈተና ገጥሞን አያውቅም::" ጀነራል አሳምነው ፅጌ:: "የትኛውንም ህዝብ በተለየ ለመጥቀም የሚሰራ ስራ የለም" ጠ/ሚ አብይ:: የሀጅ ጃዋር የረመዳን ውሎ:: የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ወላጅ አባት ህልፈት::
የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ወላጅ እባት የቀብር ስነስርአት: አህመዲን ጀበል እንደዘገበው::
መሀመድ ቢን ዛይድ የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ወላጅ አባት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ያስተላለፈው የሀዘን መግለጫ::
ሰኔ 15/ አማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ሙከራ:: የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት እና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሰጡት መግለጫ::
ጀነራል አሳምነው ፅጌ ለአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ተጠያቂ መሆናቸው ውዝግብ ማስነሳቱ:የአዲስ ፎርቹን ጋዜጠኛ መረጃ:ጀ.አሳምነው ዘንዘልማ ላይ መገደላቸው:የአብን መግለጫ እና የእነጀነራል ሰአረ ገዳይን በተመለከተ የቀረቡት አወዛጋቢ ዜናዎች::
በሰኔ15 የአብን እና ባልደራስ አባላት መታሰራቸው:: አማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከመደረጉ በፊት ሙስሊሞች በክልሉ ላይ ያነሱት ተቃውሞ:: ከሰኔ15 መፈንቅለ መንግስት በሁዋላ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ከሀገር ውጭ ቆይቶ መመለስ
የሰኔ15 መፈንቅለ መንግስት ሙከራን አስመልክቶ የአሜሪካን ኤምባሲ መግለጫ:: የአሜሪካ ወኪል በአማራ ህዝብ ላይ ያቀረበው ውንጀላ እና ዘግይቶ የጠየቀው ይቅርታ::
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የፖሊስ አደረጃጀት ለውጥ ማድረጉ::
በደቡብ የሲዳማ ክልል ጥያቄን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ቤተክርትያኖች መቃጠላቸው:ሰው መገደሉ እና ንብረት መውደሙ:አሜሪካ በወኪሏ በኩል ያስተላለፈችው መልእክት:ዴሞክራሲ ለማምጣት ቢሞከርም የጎሳ ብሄርተኝነት ሊቀንስ አልቻለም: ህገመንግስት ይሻሻል
የሲዳማ ክልል ጥያቄን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት የኢዜማ (መጀመሪያ) መግለጫ:: የኦሮሞ ብሄርተኞች ከህወሀት ጋር የፌዴራሊስት ሀይሎች በሚል ጥምረት በጋራ ለመስራት ወደመቀሌ ማምራታቸው::
በአዲስ አበባ ለመስኪድ መስሪያ ቦታዎች መታጠር መጀመራቸው:: በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ተቃውሞ:: የኦነግ ታጣቂዎች በምስራቅ ወለጋ የመንግስት ሰራተኞችን መግደላቸው:: የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ መስኪዶችን አፈረሰ በሚል የቀረበበት ክስ::
ሀጅ ጀዋር መሀመድ እና ኡስጣዝ ካሚል ሸምሱ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል አብያተ ክርስትያናት መቃጠላቸው::
በኦሮሚያ ክልል አብያተክርስትያናት መቃጠላቸውን ተከትሎ የማህበረቅዱሳን መግለጫ:: የኦሮሚያ ቤተክህነትን ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩ እና የሙስሊሞች ምላሽ::
የኦሮሚያ ቤተክህነትን ለማቋቋም የተደረገው ሙከራ ተቃውሞ ገጠመው:: የፓትሪያርኩ ምላሽ እና በቤተክርስትያን ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚያውግዙ ሰልፎች::
የቤተክርስትያን ቃጠሎን ለመቃወም የተጠሩ ሰልፎች መከልከላቸው::በጅማ የቤተክርስትያን ቃጠሎን ለመቃወም ሰልፍ በወጡ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች እና ፖሊስ መካክል ግጭት መፈጠሩ:: ንብረት መቃጠሉ እና በርካታ ክርስትያኖች ታፍነው መወሰዳቸው::
መስከረም 4/2012 በመስቀል አደባባይ የተጠራው የቤተክርስትያን ተቃውሞ ሰልፍ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ:: ከስደት የተመለሱት ፓትሪያርክ በአለ ሲመት ታስቦ መዋሉ::
ቤተክርስትያን የማንቂያ ደወል ፕሮግራሞች መጀመራቸው:: በአማራ ክልል የኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ተቃውሞ ሰልፍ:: ኢሬቻ አዲስ አበባ ላይ መከበሩ:: "የሰበረንን የነፍጠኛ ስርአት ሰብረናል::" የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት::
የሲዳማ ክልል ሪፈረንደም ዝግጅት:: በአዋሳ የከተማ ነዋሪነት መታወቂያ መታደሉ::
ኦሮሚያ ክልል ደብረዘይት ጅማ እና ሌሎችም ከተሞች የደመራና መስቀል በአል ክልከላን ተከትሎ የተፈጠሩ ግጭቶች::በአዲስ አበባ ህገወጥ ባንዲራ ያስነሳው ውዝግብ:: አዲስ አበባ መስቀል በድምቀት መከበሩ::
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት ጥቅምት 2 በመስቀል አደባባይ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የአዲስ አበባ ልዩ ፖሊስ መቋቋሙ:: አዲስ አበባ ሙስሊሞች የኢማም አህመድ ትውልድ ነን በሚል መደራጀታቸው::
የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ የኖቤል ሰላም ሽልማት:: ጠቅላይ ሚንስቴሩን ለኖቤል ሽልማት ያጫቸው ማን እንደሆነ ውዝግብ ማስነሳቱ:የአሜሪካው ወኪል በ July 23 2018 እጩነታቸው አቅርቤያለሁ ሲሉ ዶክተር አዎል አልጀዚራ ላይ በፃፉት ፅሁፍ ሌላ ብለዋል
የኦነግ ታጣቂዎች በምስራቅ ጉጂ ያደረሱት ጥቃት::በአፋር:በአማራ እና ቅማንት የተነሱ ግጭቶች:: አዲስ አበባ የኢዜማ ስብሰባ በቄሮዎች መደናቀፉ::
October 22 2019 ለሊት የሀጅ ጃዋር መሀመድ ጥበቃ ሊነሳ ነው መባሉን ተከትሎ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አዲስ አበባ መታየቱ:: የታጠቁ ቄሮዎች አዲስ አበባ መኖራቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መውጣታቸው::
የሀጅ ጃዋር መሀመድ ጥበቃ ተነሳ መባሉን ተከትሎ ቄሮዎች በአይሱዙ እየተጫኑ ወደከተሞች መላካችው:ቤተክርስትያን:ንብረት መቃጠሉ: መንገድ ተዘግቶ ክርስትያኖች አንገታቸው ላይ ባለው መስቀል እየተለዩ መደብደባቸው::
በዶዶላ እና ባሌ ሮቤ ክርስትያኖች ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ:ቄሶች እጅና አንገታቸው መቆረጡ: አብያተ ክርስትያናት መቃጠላቸው: ህወሀት ሀጅ ጃዋር መሀመድን ደግፎ ያስተላለፈው መልእክት: የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አፈሳ::
የሀጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ጉዞ:ገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረኮች: "የነፍጠኞች" ተቃውሞ: የሲዳማ ክልል በአብላጫ ድምፅ ሪፈረንደም መወሰኑ::
የዳኡድ ኢብሳ ኦነግ በምርጫ ቦርድ የምዝገባ ዘርተፍኬት ማግኘት: የኢህአዴግ መፍረስና በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተቀሰቀሰው የብሄር ግጭት::
ሙስሊሞችን እና የኦሮሚያ ቤተክህነትን ያሳተፈው የሰላም ኮንፈረንስ በኦሮሚያ:: የሀረሩ የሰላም ኮንፈረንስ:: "ጃዋርን ቀርቶ ሊገድሉን የተዘጋጁትንም አብረን እየኖርን ነው::" "ነገም አብረን እንሰራለን አብረን እንታገላለን::"
የደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መታገታቸው:: ምርጫ ቦርድ የምርጫ 2012 ሰሌዳን ይፋ ማድረጉ::
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ መመስረት::
አዲስ አበባ በሚሊንየም አዳራሽ የኦነግ ስብሰባ:: ለጥምቀት በአል ዝግጅት የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አርማ ያለባቸው ባንዲራዎች መሰቀላቸው:: በኦሮሚያ ክልል ባንዲራዎቹ በህግ አልተፈቀዱም በሚል መከልከላቸው::
አማራ ክልል ሞጣ ከተማ አራት መስኪድ "በክርስትያን መንጋዎች" "የሽብር ጥቃት" ተቃጠሉ መባሉን ተከትሎ ከንቲባ ታከለ እና ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ያስተላለፉት መልእክት::
ሞጣ መስኪድ ተቃጠለ መባሉን ተከትሎ የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ጎራዴ:የሳኡዲ አረቢያ ባንዲራ እና በውጭ ሀገር የተቃጠሉ መስኪድ ፎቶዎችን ይዘው መውጣታቸው::
የኦሮሚያ ክልል ልዩ ፖሊስ ያስመረቀው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት: በኦሮሚያ ከተሞች ወደስራ ያልገቡ ባለሀብቶች መሬት መወሰዱ:ቄሮዎች አማራ ተማሪዎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቁ እና የድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ መዘጋት::
ሀረር ድሬዳዋ: የጥምቀት በአልን ትከትሎ ታቦት አያልፍም ባሉ ቄሮዎች እና ክርስትያኖች መካክል ይተቀሰቀሰው ግጭት:: የክርስትያኖች ቤት ተቃጠለ: መከላከያ ተላከ::
የታገቱት የደምቢዶሎ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲለቀቁ የሚጠይቁ ሰልፎች::
ባልደራስ ከምርጫቦርድ ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት ማግኘቱ: የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ በደቡብ ክልል የምርጫ ቅስቀዛ ጎዞዎች እና የኢዜማ ተቃውሞ::
የኮሮና ቫይረስ ምርጫ 2012ን ማራዘሙ::

----ከመጋቢት እስከ መጋቢት----
You can follow @GurageFirst.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled: