በቅርቡ አንድ በጣም ሲኒየር የሆነ የሥራ አለቃዬ የመከረኝን ምክር ላካፍላችሁ:: ሰውየው ዕድሜ ጠገብ እና ከተቋሙ ከፍተኛ የስራ አስፈፃሚ አካላት አንዱ ሆኖ የኖረ ነው::በውል ይወቀኝ አይውቀኝ እርግጠኛ አይደለሁም ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኘን...
ምናልባት የ40 ዓመት የዕድሜም ሆነ የሥራ ልምድ ልዩነት ይኖረናል ብዬ እገምታለሁ:: የተገናኘነው እኔ የሆነ በተቋም ደረጃ ባለ ኮሚቴ ውስጥ ይሄ ሰውዬ የሚመራውን ዲቪዥ ተወካይ ሆኜ ከኮሚቴው ለቀረበ ጥያቄ ከአለቃው ምላሽ ፈልጌ ነው...
እና ከጥያቄው በፊት ስለኮሚቴው አላማ ንገረኝ ብሎኝ አስረዳሁት:: ያለፍላጎቴ እንደተሰየምኩና በኮሚቴ አባልነት ባልቀጥል ደስ እንደሚለኝ ጨምሬ አስረዳሁት:: ለምን ቢለኝ ኮሚቴው የትልልቅ ሰዎች ጥርቅም ነው (በእሱና ከእሱ በላይ ባሉ አለቆች)...
ይህንን በግልፅ አስረድቼው ከነዚህ ትልልቅ ሰዎች ጋር መሰብሰብ ምቾት እንደማይሰጠኝ አስረዳሁት::እነማን ናቸው ብሎ የተወሰኑትን ዘረዘርኩ:: በደንብ ያውቃቸዋል::ከዛ ይሄማ ቀላል ነው ዲቪዥናችንን መወከል መቀጠል አለብህ ብሎ ምክሩን ጀመረ...
ይሄ ኮሚቴ በጣም ቀላል ነው ብዙ አውሪዎች አሉበት...አንተ ማዳመጥና መማር ብቻ ነው የሚጠበቅብህ አለኝ:: በቅንነት ልምከርህ አንተ በጣም ወጣት ነህ በዛ ላይ ጥቁር ነህ ገና እዛ ክፍል ውስጥ ስትገባ በመገረም ያዩሀል እንጂ ብታወራም አይሰሙህም አለ...
ስለዚህ ዝም ብለህ አዳምጥ:ማስታወሻ ውሰድ ስለሚወራው ነገር በደንብ ተረዳ:: ስለፕሮጀክቱ የሚሰጡት አስተያየቶች/ውሳኔዎች ስህተት ቢመስሉህም ስህተት ናቸው ብለህ እንዳትጠቁም ማስታወሻ ይዘህ ወደቤት ሂድ::ለምን ስህተት እንደሆነ በደንብ አጢን...
ስህተቱ ሊስተካከል የሚችልበትን መፍትሔ አስበህ ተለዋጭ ሐሳብ ይዘህ ቅረብ::በልበ ሙሉነትና በትህትና የምታነሳው ሐሳብ እንዳለህ አስረዳና የነሱ ሐሳብ ስህተት ስለመሆኑ ሳይሆን ያንተ ተለዋጭ ሐሳብ እንዴት ውጤቱን የተሻለ እንደሚያደርግ አስረዳ...
...እንጂ ስህተታቸው ላይ ትኩረት አትሳብ::የመፍትሔ ሐሳብ ከሌለህ ደግሞ ስህተቱን ባትናገር ይመረጣል ምክኒያቱም አብዛኛው ሰው መንቀፍ ይችላል መፍትሔ የሚያመነጩ ግን ጥቂቶች ናቸው:: መፍትሔ ስታቀርብ ጥቁር መሆንህንም ይረሳሉ አለኝ እላችኃለሁ😄
You can follow @hymelee.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled:

By continuing to use the site, you are consenting to the use of cookies as explained in our Cookie Policy to improve your experience.