ይሄን ትዊት ብዙ ሰዎች ሲቃወሙ አይቻለው:: እንደ መአዛም ያክል ባይሆን ስለ ቤት ውስጥ ጥቃት ኬዞች የምናውቅ ሰዎች ለምን ይህ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ይገባናል:: ትዝ ካሉኝ ውስጥ አንዱ ባሏ ከፍተኛ ድብደባ ያደረሰባት የሁለት ቀን አራስ ነች:: https://twitter.com/ashenafi_meaza/status/1248132621533696000">https://twitter.com/ashenafi_...
ጎረቤቷ ነበረች ፌስቡክ ላይ የፃፈችልኝ:: ስልኬን ሰጠኅትና አራሷን አገናኘችኝ:: ድምጿ በጣም ዝቅ ያለ ይሁን እንጂ እርግጠኛነትዋ ግን ግልፅ ነበር:: "የኔ እህት ዛሬ ከስራ ሲመለስ እንደሚጨርሰኝ አውቃለሁ እንደምንም ብዬ ልጄን ይዤ የምሄድበት አለ?"
ጎረቤቷን አሁኑኑ ፖሊስ ጣቢያ ውሰጃት አልኳት (ማረፊያ ለማግኘት ስለሚያስፈልግ):: ጣቢያ በሌላት አቅም አንገላትዋት
https://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="☹️" title="Frowning face" aria-label="Emoji: Frowning face"> ብቻ በመጨረሻ የሴቶች ጊዜያዊ መጠለያ ገባች:: እንዲህ አይነት ሴቶች ሲመጡ ለጊዜው እነሱን መደበቅ ብቻ በቂ አይደለም::
ወንጀለኞቹ ተይዘው ፍትህ እስካላገኙ ድረስ በሰላም መኖር አይችሉም:: ያሉት ጥቂት የሴቶች መጠለያዎችም እንደሆን ከአቅማቸው በላይ የሚያስተናግዱ ናቸው:: አዳዲሶች ሲመጡ ለማሳረፍ የነባሮቹ ጉዳይ ተፍጥኖ ከመጠለያዎቹ መውጣት አለባቸው::
በዚሁ አጋጣሚ @awsadwomen ኑሩልን! ተባረኩ!
https://abs.twimg.com/emoji/v2/... draggable="false" alt="❤️" title="Red heart" aria-label="Emoji: Red heart"> የኢትዮጽያ ሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበርም (ትዊተር ላይ የሉም) እንዲህ ያሉ ሴቶችን የሚያገለግን የሴቶች ባለውለታ ድርጅት ነው:: እኔም እንደ ቤቴ የምቆጥረውና ብዙ ሴቶችን የምልክበት ቦታ ነው::
ስለዚህ መአዛን አለማክበር አልችልም:: ግን በሌላ ስራዋ ብትወቅሷት የእኔው ወገን ነች ብዬ አልከራከርላትም:: ፌሚኒስትም ሴትም ስለሆነች ሳይሆን ለፍትህ በመታገል የእኔን እድሜ የሚያክል ዘመን የስራችው ስራ ስልጣን ካሰጣት አሁንም ዳኛው ስራዋ ሊሆን
ስለሚገባ፣ ስትሳሳት መቃወሙ በጣም ጥሩ ነው! በዚህ ጉዳይ ግን እየተቃወማችሁ ያላችሁት እሷን ሳይሆን የሴቶችን መብት ስለሆነ ነው ይሄን መፃፌ:: ከ30% በላይ የሚሆኑ ኢትዩጺያዊ ሴቶች የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን በጥናቶች ተገምቷል
ከእነዚህ ውስጥ ጥቂቶች ናቸው ወደ ህግ አካል የሚመጡት፤ በአብዛኛው ህይወታቸው አደጋ ላይ ሲሆንና የሚሄዱበት ሲያጡ:: እናም በእነርሱ ላይ ለምን በር አልተዘጋም ማለት ጭካኔ ነው:: ለእነርሱ አገልግሎት መስጠት "ማሽቃበጥ" ከሆነ ሰብአዊነት ምንድነው?
Read on Twitter